የኢትዮጵያ ምክር ቤት ዛሬ ሁለት ተጨማሪ የጸረ ሽብር ህግ አጸደቀ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩንም የስድስት ወር የሥራ ዘገባ አደመጠ። ወኪላችን በላከልን ዘገባ እንዳመለከተዉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቀረቡት የሥራ ዘገባ ይዘት ይልቅ፤ በአዲሱ የከተማ ቦታ የሊዝ አዋጅ፤
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፡ መኢአድ በደቡብ ክልል በእሥር የሚገኙ አንድ መቶ አሥራ ሁለት የፓርቲው አመራር አባላት እንዲፈቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠየቀ። ኢሕአዴግ የሰላማዊውን ሂደት ምሕዳር እያጠበበ መኢአድን መንቀሳቀስ ወደማይችልበት ደረጃ አድርሶታል
በ 600 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ፤ በሰሜን ሸዋ፤ ደርባ በተባለ አካባቢ የተገነባው የስሚንቶ ኢንዱስትሪ ትናንት በጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ተመርቋል። ባለፉት 5 ዓመታት እጅግ በመጨመር በግናባታው ዘርፍ ላይ ብርቱ ተጽእኖ አሳድሮ የነበረውን የሲሚንቶ ዋጋ አዲሱ ኢንዱስትሪ ያረጋጋዋል
በይግባኝ ባይ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤና በመልስ ሰጪ ተከሳሽ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ማኅበራት ኤጀንሲ መሃል የተጀመረዉን ክርክር ዛሬ ለዉሳኔ የቀጠረዉ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፤ ሰበር ሰሚ ችሎት ዉሳኔዉን ለሌላ ቀን ቀጠረ።
በአሜሪካን የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላት፤ ዓለም ዓቀፉ የክርስቲያኖች መብት ተሟጋች ተቋምና ዓለም ዓቀፉ የመብት ተሟጋች ሂዉማን ናይትስ ዎች ታሳሪዎቹን ለማስፈታት የየበኩላቸዉን ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በተለይ በሴቶቹ ታሳሪዎች ላይ ከፍተኛ የፆታ ጥቃት መፈጸሙ ተገልጿል።
የዕለቱን ዝግጅት ለማዳመጥ የሚከተለውን ማገናኛ ይጫኑ። አስተያየታችሁ ዓቢይ ግምት የሚሰጠው ነው፤ በamharic@dw.de ላኩልን፣ በ +49-228-429-164995 ደውሉልን። በዕለቱ ዓቢይ ርዕስ ላይ በ+49 172 26 66 944 SMS አስተያየት ላኩልን። 16:00 - 17:00 UTC የአንድ ሣምንቱ የስርጭት ኮሮጆ በዚህ ሊንክ ይገኛል።