1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አደገኛው የኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰት

እሑድ፣ ሚያዝያ 13 2016

ወደ ሳዑዲ አረብያ ለመሄድ ጉዞ የጀመሩ 38 ኢትዮጵያውያን ጅቡቲ ድንበር አቅራቢያ የተጫኑበት ጀልባ ሰጥሞ ባለፈው ሳምንት ሞተዋል። በዚሁ ሳምንት ነበር ሳዑዲ አረብያ ውስጥ ችግር ላይ የወደቁ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ጥረት የቀጠለው።በአሁኑ ጊዜ በአደገኛ ጉዞ መላልሰው ወደ መካከለኛው ምሥራቅና ወደ ደቡብ አፍሪቃ የሚሄዱ ጥቂት አይባሉም።

https://p.dw.com/p/4ezUe
ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የመን ከጀልባ እንደወረዱ
ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የመን ከጀልባ እንደወረዱምስል Nariman El-Mofty/AP/picture alliance

አደገኛው የኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰት

በቅርቡ 170 ኢትዮጵያውያን ወደ የመን ለመሻገር ጀልባ ሲሳፈሩ ሶማሌላንድ ላይ ተይዘዋል። ባለፈው ሳምንት ወደ ሳዑዲ አረብያ ለመሄድ ጉዞ የጀመሩ 38 ኢትዮጵያውያን ጅቡቲ ድንበር አቅራቢያ የተጫኑበት ጀልባ ሰጥሞ ሞተዋል። በዚሁ ሳምንት ሳዑዲ አረብያ ውስጥ ችግር ላይ የወደቁ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ጥረት ቀጥሏል። የኢትዮጵያ መንግሥት በመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራትና በተለያዩ የአፍሪቃ ሀገራት እሥርን ጨምሮ በተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ የጀመረው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ነው።

የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሰቆቃ በሳዑዲ እስር ቤቶች ከየሀገራቱ መንግሥታት ጋር በሚደረግ ስምምነት ኢትዮጵያውያን በሕጋዊ መንገድ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት እንዲሄዱ በተጀመረ አሰራር ፍልሰተኞች የሚገጥማቸውን ችግር ለመቀነስ እየጣረ መሆኑንም ይናገራል። ይሁንና ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኃላ ዳግም በተመሳሳዩ አደገኛ ጉዞ እየፈለሱ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሀገራትና ወደ ደቡብ አፍሪቃ ለመግባት የሚሞክሩ  ጥቂት አይባሉም። መደበኛ ያልሆነ በሚባለው በዚህ መንገድ በሚካሄደው ፍልሰት ሞትና እንግልትም አሁንም እንደቀጠለ ነው። የመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ይዞታ

መንግሥት ከሳዑዲ አረብያ ወደ ኢትዮጵያ የመለሳቸው ስደተኞች
መንግሥት ከሳዑዲ አረብያ ወደ ኢትዮጵያ የመለሳቸው ስደተኞችምስል EDUARDO SOTERAS/AFP

አደገኛው የኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰት የዛሬው እንወያይ ትኩረት ነው። በዚህ ውይይት ላይ የሚሳተፉ አራት እንግዶች ጋብዘናልበማላዊ የኢትዮጵያውያን ስደተኞች አበሳ እነርሱም ደረጀ ተግይበሉ በኢትዮጵያ ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከልና የተመላሽ ዜጎች ድጋፍና ክትትል መሪ አስፈጻሚ ፣አቶ ኮስሞስ ገብረ ሚካኤል በደቡብ አፍሪቃ ለኢትዮጵያውያን ስደተኞች የሕግ ማማከር አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት ባለቤት አቶ ነብዩ ሲራክ ለብዙ ዓመታት ሳዑዲ አረብያ የኖረ የቀድሞ የዶቼቬለ ዘጋቢ እንዲሁም ወይዘሮ አዚዛ አሊ በአንድ የሳዑዲ ስራና ሰራተኛ አገናኝ ድርጅት በአስተርጓሚነት የሚሰሩ ኢትዮጵያዊት በጉዳዩ ላይ ተወያይተዋል።

ኂሩት መለሰ