የአፍሪቃ ኤኮኖሚ ዕድገት በዓለምአቀፉ የኤኮኖሚ ቀውስ ሳቢያ ጋብ ቢልና በወቅቱም በኤውሮ-ዞን ችግር ተጽዕኖ ቢደቀንበትም በዕርምጃው እንደሚቀጥል ነው የሚታመነው።
የኢትዮጵያ ምክር ቤት ዛሬ ሁለት ተጨማሪ የጸረ ሽብር ህግ አጸደቀ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩንም የስድስት ወር የሥራ ዘገባ አደመጠ። ወኪላችን በላከልን ዘገባ እንዳመለከተዉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቀረቡት የሥራ ዘገባ ይዘት ይልቅ፤ በአዲሱ የከተማ ቦታ የሊዝ አዋጅ፤
በሰሜን ናይጀሪያ በእርሳስ ማዕድን ብናኝ የተመረዙ በሺህ የሚቆጠሩ ሕፃናት አስቸኳይ ሕክምና እንደሚያስፈልጋቸው ለሰብዓዊ መብት መከበር የሚሟገተው ድርጅት፣ ሂውማን ራይትስ ዎች ትናንት ያወጣው አንድ ጥናት አስታወቀ። የሂውማን ራይትስ ዎች የጤና ተመራማሪ ወይዘሮ ጄን
የፍልስጤም ተቀናቃኝ ኃይሎች ፋታህና ሃማስ በመጪዉ ግንቦት ወር ምርጫ ለማካሄድ በመወሰን፤ አብሮ ለመሥራት ስምምነት መፈራረማቸዉ እስራኤልን አስቆጥቷል። ኳታር ዶሃ ላይ ከትናንት በስተያ ስምምነቱ ሲደረስ፤ እስራኤል በበኩሏ ከፍልስጤም ጋ የተጀመረዉ
ሩሲያ ያልተቀበለችዉን ረቂቅ የሚተካ ሌላ ረቂቅ ለፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት አባላት አሰራጭታም ነበር።በዩናይትድ ስቴትስ ዘነድ ተቀባይነት አላገኘም።እነዚሕ ሁለቱ ሐገራት ድምፅን በድምፅ የመሻር ሥልጣናቸዉን እንዲጠቀሙ እንደምክንያት ከሚጠቀሱ ምክንያቶች ጥቂቶቹ ናችዉ።
ብዙሃኑ የአውሮፓ ሕብረት ዓባል መንግሥታት መሪዎች ብራስልስ ላይ ባካሄዱት ጉባዔ ከትናንት በስቲያ ጥብቅ የበጀት ቁጥጥርን በሚያሰፍን አንድ ውል ለመስማማት በቅተው ነበር።
የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ፤ ኮምፒዩተራቸውን ከፍተው ከአንድ ድረ ገጽ ወደሌላው ያላንዳች ሳንክ መሸጋገር ፤ መቃኘት፣ ሐሳብ መለዋወጥ ፣ ማንበብ ፣መጻፍም ሆነ ሙዚቃ ወይም ሌላ ማድመጥ የሚችሉበት ፣ አስተማማኝ መላ የማግኘቱ ሁኔታ ፤ ቀደም ባለው ጊዜ ፤ በይበልጥም በአሁኑ ዘመን ፤ በመረጃ ሥነ ቴክኒክ ረገድ፣ ትልቅ ግምት ሆኗል የሚሰጠው።
የሴትን ልጅ ግርዛት ለማስቀረት የተጀመረዉ ዓለም ዓቀፍ ዘመቻ በየዓመቱ በጎርጎሮሳዉያኑ የዘመን ቀመር Feb 6 ቀን ይታሰባል። ዕለቱ ትናንት ሲታሰብ፤ የሴትን ልጅ የመዋለጃ አካል የመተልለቱ ተግባር በዓለማችን የ140 ሚሊዮን ታዳጊ ልጃገረዶችና፤
የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ሰንበቱን ወደ ግማቭ ፍጻሜው ቭግግር አድርጓል። ይሄው ትናንትና ከትናንት በስቲያ የተካሄደው ሩብ ፍጻሜ ዙር ግን የሚያሳዝን ሆኖ ለአስተናጋጆቹ ሃገራት ለኤኩዋቶሪያል ጊኒና ለጋቡን የስንብትም ነው የሆነው።
ዴሞክራሲንና ፍትሓዊነትን የሚያበረታታው መንግሥታዊ ያልሆነ የሀንሪኽ በል ድርጅት በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ መልካም ኑሮ የመኖር መብት ሊከበር ይገባል በሚል ርዕስ ሥር ሰሞኑን አንድ የሥዕል ትርዒት በርሊን ላይ አዘጋጅቶዋል። አሥራ አምስት ቀኖች፤
የዕለቱን ዝግጅት ለማዳመጥ የሚከተለውን ማገናኛ ይጫኑ። አስተያየታችሁ ዓቢይ ግምት የሚሰጠው ነው፤ በ +49-228-429-164995 ደውሉልን። በዕለቱ ዓቢይ ርዕስ ላይ በ+49 172 26 66 944 SMS አስተያየት ላኩልን። የአንድ ሣምንቱ የስርጭት ኮሮጆ በዚህ ሊንክ ይገኛል።
amharic@dw.de
በማዳመጥ መማር የተባለው የዶቼ ቬለ አዲሱ የመገናኛ ብዙሃን የርቀት ትምህርት በሁሉም የአህጉሪቱ ክፍሎች እውቀትን ለማዳረስ ይጥራል። »
ግሎባል አይዲያስ