1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዕጣ ፈንታ

እሑድ፣ ሚያዝያ 6 2016

ኢትዮጵያ ውስጥ የተቃውሞ ፓርቲዎች ህልውና አነጋጋሪ ከሆነ ሰነባበተ። ለእንቅስቃሴያቸው መዳከም አብዛኞቹ የገዢውን ፓርቲ የተጠናከረ ጫና በዋናነት ሲገልጹ፤ የራሳቸው የፓርቲዎቹ እራስን እየተቹና እያረሙ የማደግ ድክመትም ለውጪው ጫና ተጋላጭ እንዳደረጋቸው በምክንያትነት የሚያነሱም አሉ።

https://p.dw.com/p/4ei1P
አዲስ አበባ አንድነት ፓርክ
አዲስ አበባ አንድነት ፓርክምስል Azeb Tadesse Hahn/DW

በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዕጣ ፈንታ

 

ኢትዮጵያ ውስጥ የተቃውሞ ፓርቲዎች ህልውና አነጋጋሪ ከሆነ ሰነባበተ። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በከፋ መልኩ ኅብረተሰቡ ከተለያዩ አካባቢዎች በልዩ ልዩ ምክንያቶች ሲፈናቀል፤ በሀገሪቱ የሰላማዊ ዜጎች ግድያና ሞት ከመደጋገሙ የተነሳ የተለመደ ክስተት እየሆነ ወደመምጣቱ ሲሸጋገር፤ የኑሮ ውድነቱ ከዜጎች ገቢ በላይ ንሮ ብዙሃኑን ለምጽዋት ጠባቂነት ሲዳርግ፤ በእርግጥ የህዝቡን ሕመም የሚታመሙ፤ ችግሩንም በአደባባይ የሚያስተጋቡ ፖለቲከኞች የትገቡ የሚለው ጥያቄ ይነሳል።

በ2010 መጋቢት ወር ማለቂያ አንስቶ የተሻለ አስተዳደርና በፖለቲካው በኩልም ትርጉም ያለው ቁጥጥርና ሚዛን የማስጠበቃቸው ሚና ተጠናክሮ ለማየት የነበረው ጉጉት፤ አሁን ምኞች ብቻ ሆኗል። ዛሬ ከኢትዮጵያ የሚሰማው የብዙሃን ሞትና ስደት፤ የዜጎች ከያለበት መፈናቀል፤ ከአንድ ጦርነትና ግጭት ወደ ሌላው፤ የመሻገሩ ማለቂያ የሌለው አዙሪት የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቧል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የፓርቲዎች ውይይት

ችግሩን እየነቀሱ እርምት እንዲደረግ የሚጠይቁ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፈጽሞ የሉም ባይባልም ከብዛታቸው አንጻር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። በዚህ በመነሳትም ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉም የሉምም ከሚያስብል ደረጃ ደርሰዋል።

የተቃውሞ ፖለቲካ ፓርቲዎቹ እንቅስቃሴ ለመዳከሙ በምክንያትነት አብዛኞቹ የገዢውን ፓርቲ የተጠናከረ ጫና በዋናነት ሲገልጹ፤ የራሳቸው የፓርቲዎቹ እራስን እየተቹና እያረሙ የማደግ ድክመትም ለውጪው ጫና ተጋላጭ እንዳደረጋቸው የሚያነሱም አሉ።

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስሞታ

በዚያም ላይ የኅብረተሰቡ ከምን በላይ የምሁራን የፖለቲካ ተሳትፎ ውስን መሆን በሀገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለመዳከማቸው መንስኤ እንደሆነም ያስረዳሉ። በኢትዮጵያ የፖለቲካ አውድ የተቃውሞ ፖለቲካው ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን? በቀጣይስ እራሳቸውን በተፎካካሪነት ለምርጫ የማቅረብ አቅማቸው እንዴት ይታያል? የሚለው የዕለቱ የመወያያ እርዕሳችን ነው።

ሦስት እንግዶችን ለውይይት ጋብዘናል፤ አቶ ደስታ ዲንቃ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ የኦዲት እና ኢንስፔክሽን ሃላፊ እንዲሁም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ፤ መጋቢ ብሉይ ሃይማኖት አብርሃም የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ኢሕአፓ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት እንዲሁም እንዲሁም ለረዥም ዓመታት በተቃውሞ ፖለቲካው የዘለቁት አቶ ልደቱ አያሌው ናቸው።

ሙሉውን ውይይት ያድምጡ

ሸዋዬ ለገሠ