የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን በመጪው 2014 ዓ-ም ብራዚል ውስጥ ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ውድድር ለመድረስ በሚደረገው የአፍሪቃ ማጣሪያ ትናንት ደቡብ አፍሪቃን 2-1 በማሸነፍ የምድቡን አንደኝነት ማረጋገጡ አይዘነጋም።
በአውሮፓ ቀደምት የእግር ኳስ ሊጋዎች ውስጥ የክረምቱ ዕረፍት ተጠናቆ ሁለተኛው ዙር ውድድር የሚከፈትበት ጊዜ እየተቃረበ ሲሆን የተለያዩት ክለቦች ሞቃት በሆኑት የደቡብ አውሮፓ አካባቢዎች ዝግጅታቸውን ጀምረዋል።
ብራዚል ውስጥ በሚቀጥለው የጎርጎሮሳውያኑ 2014 ዓ-ም ለሚካሄደው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ፍጻሜ ውድድር ዙር ለማለፍ ሰንበቱን ከአፍሪቃ እስከ አውሮፓና ላቲን አሜሪካ በርካታ ማጣሪያ ግጥሚያዎች ተካሂደዋል።
የ68 ዓመቱ የኤፍ ሴ ባየርን ሚውንኽኑ የእግር ኳስ ክለብ አሠልጣኝ ዩፕ ሀይንከስ በቀጣዩቹ የቡንድስሊጋ የግጥሚያ ወራት ዕረፍት እንደሚያደርጉ ትናንት በይፋ አስታወቁ።
የዕለቱን ዝግጅት ለማዳመጥ 16:00 - 17:00 የሚለውን ማገናኛ ይጫኑ። የአንድ ሣምንቱ የስርጭት ኮሮጆም "ዝግጅት"ን በመጫን ሊገኝ ይችላል። የአማርኛ፣ የኪስዋሂሊ፣ የሀውሳ፣የእንግሊዝኛ፣ የፈረንሣይኛ እና የፖርቱጊዝኛ ቋንቋ ሥርጭትን በሚተላለፍበት ጊዜ በኢንተርኔት በInternet Explorer 8 በቀጥታ ማድመጥም ይቻላል።
በማድመጥ መማር እያዝናና መረጃ የሚሰጥ ዝግጅት ነው።