1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኪነ ጥበብአፍሪቃ

ብዙ ተስጥዖ ያላት ቬንስያ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 4 2015

ቬንስያ ኤፍሬም 16 ዓመቷ እና የ10ኛ ክፍል ታዳጊ ናት፡፡ ነዋሪነቷን አዳማ ከተማ ያደረገችው ቬንስያ የውኃ ዋና እና ስዕል መሳል በጣም ያስደስቷታል። በግሏ በምታደርገው ጥረት የዋና ችሎቷዋን ያዳበረችው ቬንስያ፤ ይህ ክህሎቷ ሁነኛ መዝናኛዋ እና የሰውነት ማጎልበሻ ስፖርት እንደሆናት ታነሳለች፡፡

https://p.dw.com/p/4PwqO

ከዋና ችሎታዋ በተጨማሪ እያጎለበተች በመጣችው የተለያዩ ስዕሎች (Abstract Pictures) የመሳል ችሎታዋ እና ጌጣጌጥ ብሎም ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ የጥበብ ስራዎችን በራሷ ፈጠራ ታሰናዳለች፡፡

ወደ ፊትም ትምህርቷን በዲዛይነርነት በማዳበር ታዋቂ የፋሽን እና ዲዛይን ባለሙያ መሆን ታልማለች። ለዚያም የሚሆን ጥርጊያ መንገድ ስለመያዟም ታብራራለች፡፡

ቬንስያ ህይወትን ለማሸነፍ በርካታ የህይወት አማራጮችን መያዝ ያለውን ፋይዳም አጉልታ ነው የምታስረዳው፡፡#ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘጋባ፡ ሱመያ ሳሙኤል

ቪዲዮ፡ ሥዩም ጌቱ