1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የመቐለ ጉዞ

ማክሰኞ፣ ጥር 2 2015

አትሌት ለተሰንበት ግደይ፣ ጎተይቶም ገብረሥላሴ እና ጉዳፍ ፀጋይን ጨምሮ ሌሎች አትሌቶችና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አመራር ዛሬ መቐለ ገቡ። በመቐለ አሉላ አባነጋ ዓለምአቀፍ ኤርፖርት በነበረ አቀባበል የአትሌቶቹ ቤተሰቦች፣ የክልሉ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች፣ ስፖርተኞች እና ሌሎች ተገኝተው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

https://p.dw.com/p/4LyVd
Äthiopien Sportler aus Tigray in Mekele angekommen
ምስል Million Hailesilassie/DW

ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል

አትሌት ለተሰንበት ግደይ፣ ጎተይቶም ገብረሥላሴ እና ጉዳፍ ፀጋይን ጨምሮ ሌሎች አትሌቶችና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አመራር ዛሬ መቐለ ገቡ። በመቐለ አሉላ አባነጋ ዓለምአቀፍ ኤርፖርት በነበረ አቀባበል የአትሌቶቹ ቤተሰቦች፣ የክልሉ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች፣ ስፖርተኞች እና ሌሎች ተገኝተው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። 

በአትሌት ደራርቱ ቱሉ የተመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ልኡክ ቡድን ዛሬ መቐለ ከተማ የደረሰው የትግራይ ክልል ተወላጅ የሆኑ አትሌቶችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማገናኘት እንዲሁም በትግራይ ክልል ያለውን የአትሌቲክስ እንቅስቃሴ ለማነቃቃት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

Äthiopien Sportler aus Tigray in Mekele angekommen
አትሌቶቹ ትግራይ ክልል መቐለ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፤ ከቤተሰብም ጋር ተገናኝተዋልምስል Million Hailesilassie/DW

ለረዥም ጊዜ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተለያይተው የቆዩት እነዚህ የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዛሬው የመቐለ ጉብኝታቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲሁም ከቀድሞ የቡድን አጋሮቻቸውና ከአድናቂዎቻቸው ጋር ተገናኝተዋል።

አትሌት ለተሰንበት ግደይ፣ ጎተይቶም ገብረሥላሴ እና ጉዳፍ ፀጋይ በኦሬገኑ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክለው በመወዳደር ከፍተኛ ውጤት ማግኘታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በወቅቱ ትግራይ ክልል ከሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘት አለመቻላቸውን ገልጠው ነበር። 

ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ወደ ትግራይ የአውሮፕላን በረራን ጨምሮ የተለያዩ የግንኙነት መስመሮች በመከፈታቸው አትሌቶቹ እንዲሁም ሌሎች በርካቶች ከሁለት ዓመት በኋላ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እየተገናኙ ነው።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ