1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመጋቢት 23 ቀን 2016 የስፖርት መሰናዶ

ሰኞ፣ መጋቢት 23 2016

በሰርቢያ ዋና ከተማ ቤልግሬድ በተካሔደው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች። የቀደሞው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ግዛው ተክለማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የዛሬው የስፖርት መሠናዶ ይኸን ጨምሮ በሣምንቱ መጨረሻ የተካሔዱ የእግር ኳስ እና የሜዳ ቴኒስ ጨዋታዎችን ይዳስሳል።

https://p.dw.com/p/4eJoj
ማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል ጨዋታ
ማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል እሁድ ባደረጉት ጨዋታ አቻ በመለያየታቸው ሊቨርፑል የፕሪምየር ሊግ መሪ ሆኗል። ምስል Dave Thompson/AP Photo/picture alliance

የመጋቢት 23 ቀን 2016 የስፖርት መሰናዶ

በሰርቢያ ቤልግሬድ በተካሄደው የሀገር አቋራጭ የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያ በሁለተኛ ደረጃ አጠናቃለች። ኢትዮጵያ 2 ወርቅ 6 ብር እና 2 ነሃስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች። 

በወጣት ሴቶች የ6 ኪሎ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት በመውጣት አሸንፈዋል። በተመሳሳይ በወጣት ወንዶች 8 ኪሎ ሜትር ውድድር የብር ሜዳሊያ አግኝታለች። እንዲሁም በድብልቅ ሪሌ 8 ኪሎ ሜትር ውድድር የብር ሜዳሊያ ስታገኝ በአዋቂ 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ግን ኬንያውያን አትሌቶች የበለይነትን አግኝተው አጠናቀዋል።

ዜና ረፍት

የቀደሞው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ግዛው ተክለማርያም ከዚህ አለም በሞት የተለዩ።  የእግር ኳስ ፌዴሬሽንን በፕሬዚዳንትነት የመሩት ኢንጂነር ግዛው ተክለማርያም የታዳጊ ወጣቶች ሥልጠና ፕሮጀክቶች እንዲመሠረት አድርገዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየርና ሊግ እና ብሔራዊ ሊግ ከመሰረቱት መካከል ነበሩ ይህ ብቻ ሳይሆን ፣ የሴቶች እግር ኳስ እንዲጀምር፣ የአፍሪካ ወጣቶች ዋንጫ በኢትዮጵያ እንዲስተናገድ ባደረጉት ጥረት ይታወሳሉ። 

ኢንጅነር ግዛው ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት የነበሩ ሲሆን በተወለዱ በ80 ዓመታቸው መጋቢት 19 ቀን 2016 በጴጥሮስ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።

የመጋቢት 16 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

በባሕር ዳር ከነማ እግር ኳስ ታሪክ "23" ቁጥር ማልያ ከዚህ በኋላ የማይለበስ ሆኗል

የባሕር ዳር ከነማ ስፓርት ክለብም ከዚህ በኋላ ኮከቡ ለነበረው ተጫዋቹ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ "23" ቁጥር ማልያ እንዳይለበስ ሲል ውሳኔ አስተላልፏል። 
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የባሕር ዳር ከተማ የመሐል ሜዳ ተጫዋች የሆነው አለልኝ አዘነ ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቹ አርባ ምንጭ ከተማ በሄደበት ድንግት ከዚህ ዓለም በሞት መለይቱ ይታወሳል።

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ የባሕር ዳር ከነማ እግር ኳስ ክለብ ቡድን አባላት እና አመራሮች አርባ ምንጭ በሚገኙት የአለልኝን ቤተሰቦች ማፅናናታችው ተነግሯል። ከዚህ ኮከብ ከነበርው ወጣት ተጫዋች ህልፈተ ህይወት ጋር ተያየዞ ፖሊስ ቤተሰቦቹን በህግ ቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማድረግ ላይ መሆኑ ተሰምቷል።

የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ

ማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል በኢትሀድ ባደረጉት ጨዋታ
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል በኢትሀድ ባደረጉት ጨዋታ 0ለ0 ተለያይተዋል።ምስል Dave Thompson/AP Photo/picture alliance

በሳምንቱ መጨረሻ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ከተደረጉት 10 ጨዋታዎች ማንችስተር ሲቲ ከአርሰናል ሊቨርፒል ከብራይተን በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቁ ነበር። በ30ኛ ሳምንቱ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ትላንት በኢትሀድ የተስተናገደው የማንችስተር ሲቲ እና የሰሜን ለንደን አርሰናል ጨዋታ ከተጠበቁት የፕሪምየር ሊጉ የሳምንቱ ጨዋታዎች መከከል አንዱ ነበር። ሁለቱም ቡድኖች ሳይሸናነፉ ባዶ ለባዶ በመለያየታቸው የፕሪምየር ሊጉን የመሪነት ስፍራ ለ ሊቨርፑል አሳልፈው ለመስጠት ተገደዋል።

በፕሪምየር ሊጉ በመሪነት ሊያስነብተው የሚያስችል ነጥብ ይዞ ለመውጣት ወደ ማንችስተር ሲቲ ተጉዞ የነበረው አርሰናል በነበረው ጨዋታ ባዶ ለዳዶ ተለያይቶ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቶዋል። የጨዋታው ጊዜ ሲጠናቀቅ 65 ነጥብ የያዘው የአርሰናሉ ሚኪል አርቴታ ከ ፔፕ ጋርዲዮላ በተሻለ እርካታ ከሜዳ የወጡ ይመስላል።

ትላንት በተደረገው ሁለተኛ ጨዋታ የርገን ክሎፕ ቡድን ተጋጥመውን ብቻ ሳይሆን ያሸነፈው የፕሪምየር ሊጉን የደረጃ ሰኝጠረዥ በ 67 ነጥብ እንዲመራ አስችሎታል። 61 ሺሕ 276 ተመልካቾችን በሚይዘው አንፊልድ በተደረገው የሊቨርፑል እና የብራይተን ጨዋታ በሊቨርፖል 2 ለ1 አሸነፊ ነው።

የየርገን ክሎፕ ቡድን ጨዋታው በተጀመረ በሁለተኛው ደቂቃ ዳኒ ዌልቤክ ባስቆጠረው ጎል ሲመራ የቆየው ለ25 ደቂቃ ብቻ ነበር።  በ27ኛው ደቂቃ ሉዊስ ዲያዝ አማካኝነት አቻ ሆኑ። ብራይተኖች ዳግመኛ መሪነቱን ለመያዝ ጠንካራ ግፊት ቢያደርጉም ሳይሆንላቸው 1 ለ 1 በሆነ ውጤት እረፍት ወጡ። ከረፍት መልስ ሊቨርፑሎች በፈጠሩት ግፊት 65 ኛው ደቂቃ ላይ መሀመድ ሳላህ ሁለተኛውን ጎል አስቆጥሮ 2 ለ 1 መምራት ጀመሩ።

ብራይተኖች በራቸውንም መጠበቅ አልያል የተጋጣሚያቸውን በር መክፍት ሳይችሉ ቀርተው 2 ለ 1 ተሸንፈዋል። በትላንቱ ጨዋታ ሊቨርፑልም ፕሪምየር ሊጉን በ 67 ነጥብ በመሪነት እንዲይዝ አስችሎታል።

የርገን ክሎፕ
የርገን ክሎፕ የሚመሩት ሊቨርፑል በ67 ነጥብ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን በመምራት ላይ ይገኛል። ምስል CSM/ZUMA Press Wire/dpa/picture alliance

ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ በተደረጉት ተመሳሳይ የ30ኛ ሳምንት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ኒውካስል ዊስትሀም ዩናይትድን 4 ለ 3 ፣ አስቶን ቪላ ዊልቨርሀምተንን 2 ለ 0 ሲረቱ በርንማውዝ ኤቨርተንን ፣ቶተንሀም ሆትስፕር ሉተንን በተመሳሳይ 2 ለ 1 አሽንፈው 3 ነጥብ ይዘው ወጥተዋል። ማንችስተር ዩናይትድ ከ ብሪንትፎርድ ክርስታል ፓላስ ከ ኖቲግሀም ፎረስት 1 ለ 1 ቸልሲ ከበርንሊይ 2 ለ 2 በመለያየት ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል።

የመጋቢት 9 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

በመሆኑም በ 30ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የጨዋታው መርሀ-ግብር ውጤት መሰረት ፕሪምየር ሊጉን ሊቨርፑል በ67 ነጥብ ሲመራው አርሰናል በሁለት ነጥብ ዝቅ ብሎ በ65 ነጥብ ሁለተኛ ማንችስተር ሲቲ በ64 ነጥብ ሶስተኛ ሆነው ይከተላሉ. ሉተን በ20 ብርንሌይ በ18 ነጥብ የወራጅ ቀጠናውን ይዘዋል ።

ቡንዲስ ሊጋ

በ27ኛው ሳምንት ጀርመን ቡንደስሊጋ የእግር ኳስ ግጥሚያ መርሀ-ግብር አሁንም ባዬርን ሌቨርኩሰን ከድል የሚያስቆመው አልተገኘም። ቅዳሜ ዕለት ተጋጥመው ሆፊንሀምን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ረትተዋል። በጨዋታው ጎል ከመረብ የማሳረፉን ቅድሚያ የያዙት ሆፊንሀሞች ቢሆኑም የቡንደስ ሊጋው መሪው ባዬርን ሌቨርኩሰን ባደረገው መልሶ ማጥቃት የጨዋታው አሸናፊ ሆኗል።

በቀጣዩ የጨዋታ ዘመን ቡድኑን ሊለቁ ይችላሉ ሲባል የሰነበተው አሰልጣኝ ዣቪ አሎንሶ ከሊቨርኩሰን ጋር እንደሚቆዩ ካስታወቁ በኋላ በተደረገው በዚህ የመጀመሪያ ጨዋታ ውጤት በርካቶችን አስደስቶዋል ።

ባየር ሙኒክ በቦሩሲያ ዶርትሙንድ 2 ለ 0 ተረቷል። ለወትሮው የቦንደስ ሊጋው መሪ እና አሽናፊ በመሆን የሚታወቀው ባየር ሙኒክ ተስፋው ያከተመ ይመስላል።  ቡንድስ ሊጋው በቀረው 7 ጨዋታ እና በ መሪው ባየር ሊቨርኩሰን 13 ነጥብ ብልጫ ልዩነት የዘንድሮ የቡንዲስ ሊጋ የዋንጫ ህልም እውን የሚሆን አይመስልም።

የቦሩሺያ ዶርትሙንድ ተጫዋቾች
በጀርመን ቡንደስ ሊጋ ባየር ሙኒክ በቦሩሺያ ዶርትሙንድ ተሸንፏል። ምስል Tom Weller/dpa/picture alliance

ትላንት እሁድ በተለያዩ ከተሞች ተስተናገደው የቡንዲስ ሊጋ 3 ጨዋታዎች ሁሉም በ አቻ ነጥብ ተጠናቋል። አጉስ በርግ ከ ኮሎኝን 1 ለ 1 ስቱት ጋርት ሁፍንሀም 3ለ3፣ቦሁምን ከ ዳርምሽታድ 2 ለ 2 በሆነ አቻ እጥዒት ተለያይተው ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል።

የጀርመን ቡንዲስ ሊጋ የደረጃ ሰንጠረዥ ባዬርን ሊቨርኩሰን የቅዳሜ ድሉን ጨምሮ እስካሁን ባለው 73 ነጥብ ቡንደስ ሊጋውን በአንደኛነት ይመራል። በተቃራኒው በቅዳሜ እለቱ ጨዋታ ሽንፈት ያስተናገደው ባየር ሙኒክ በ13 ነጥብ ልዩነት በ60 ነጥብ ሁለተኛ ነው። ሽቱትጋርት 57 ነጥብ ሰብስቦ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በወራጅ ቀጠናው ማይንትስ በ20 ነጥብ16ኛ ደረጃን ሲይዝ ኮሎኝ በ19 ነጥብ አስራ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ዳርምሽታድ በ14 ነጥብ ወራጅ ቀጠናው ግርጌ ላይ ይገኛል።

ስፔን ፕሪምየር ሊጋ

ሪያል ማድሪድ በሻንፒዮንስ ሊግ ማንችስተር ሲቲን ከመግጠሙ በፊት ያደረገው ጨዋታ  አትሊቲኮ ቤልባኦን 2 ለ 0  በማሽነፍ በድል ተጠናቋል። ብራዚላዊው አጥቂ ሮድሪጎ ጨዋታ በተጀመረ በ8ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል 1 ለ 0 ረፍት የወጡት ሁለቱ ቡድኖች ከረፍት መልስም በ73 ኛው ደቂቃ አሁንም ሮድሪጎ ከመረብ ባሳረፈው ጎል ጨዋታው ተጠናቋል። ሪያል ማድሪድ በአትሌቲኮ ቤልባኦ ላይ ያስመዘገበው ድል አሁንም ላሊጋውን በ75 ነጥብ በመሪነት እንዲቀጥል አስችሎታል።

የመጋቢት 2 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ባርሴሎና  ላስ ፓልማስን 1 ለ 0 በመርታት የደረጃ ሰንጠረዡን በ ሁለተኛነት እንደያዘ ቀጥሎዋል። ሲቪላ ጌታፌን 1 ለ 0 አሸንፏል። ኦሳሱና  አለ ማሪያም 3 ለ 0 ቫሊንሲያ እና ማሎርካ  ሲልታ ቪጎ ከ ራዮ ቮልካኖ   በተመሳሳይ 0 ለ 0 ተለያይተው ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል። በሳምንቱ መጨረሻ በተደረጉ የስፔን ፕሪምየር ሊጋ ጨዋታዎች ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና ተጋጣሚዎቻችውን በመርታት የ ላሊጋውን የደረጃ ሰንጠረዥ እንደያዙት ይገኛሉ። ሪያል ማድሪድ በ75 ነጥብ ይመራል ባርሴሎና በ 67 ነጥብ ይከተላል።
 
የሜዳ ቴንስ

ቅዳሜ እለት በተካሄደው የሚያሚ ኦፕን የሜዳ ቴንስ ጨዋታ አሜሪካዊቷ  ዳኒኤላ ኮሊንስ  ሩሲያ የተወለደችው ካዛኪስታነዊትዋን  ኢሊና  7 ለ 5 6 ለ 3 በአጠቃላይ 2 ለ 0 በመርታት አሽናፊ ሆናለች። በተመሳሳይ በወንዶች ሲነር ግሪጎሮ ዲሞትሪቪን 6 ለ 3 እና 6 ለ 1 በአጠቃላይ 2 ለ 0 በማሽነፍ የ ሚያሚ ኦፕን የወንዶች የሜዳ ቴኒስ አሽናፊ ሆነዋል።

ሐና ደምሴ 

እሸቴ በቀለ