1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኪነ ጥበብአፍሪቃ

የኬንያ ሚኒባስ ታክሲ ወያላዎች ትርዒት

ረቡዕ፣ ሐምሌ 19 2015

'ማታቱ ሰርፊንግ' የሚባለው በኬንያ እየተዘወተረ የመጣ ትርዒት ነው። ግርግር በሚበዛባቸው የናይሮቢ ጎዳናዎች እና ጢም ብለው በሞሉ ሚኒባስ ታክሲዎች ወይም ማታቱዎች ላይ ወያላዎች ተንጠልጥለው ወይም ሲወርዱ አክሮባት ይሰራሉ። ከእነዚህ አንዱ ካሳያ ሙዮቲ ይባላል።

https://p.dw.com/p/4UPbn

በአንድ ጉዞ 1 ዶላር ያገኛል። «ማታቱ ላይ ትርዒት ሳሳይ ቢያንስ ሁለት ወይም ሶስት መንገደኞችን እማርካለሁ። »የሚለው ሙዮቲ አደጋው ብዙም አይታየውም።

ምንም እንኳን ልምድ ያካበቱ የማታቱ ወያላዎች የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን የሚያስደምሙ ትርዒቶች ቢያሳዩም ጎዳናውን ለሚጋሩ ሰዎች ስጋት መፍጠራቸው አልቀረም።

የትራንስፓርት እና መንገድ ባለሙያ ኦዲሃምቦ ኦቲኖ «እንደዚህ አይነት ሰዎች ከባድ ቅጣት ሊጣልባቸው ይገባል። »ይላሉ።