1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች

ረቡዕ፣ ግንቦት 16 2015

አዲስ አበባ የሚገኘው የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የተለያዩ ተስጥኦ ያላቸው ወጣቶችን ከመላው ሀገሪቱ አሰባስቦ በተለያዩ የስፖርት ዘርፎች በማሰልጠን ያበቃል፡፡ በዚህ አካዳሚ ስልጠና ከሚሰጥባቸው የስፖርት ዘርፎች ደግሞ የቴክዋንዶ ስፖርት ተጠቃሽ ነው፡፡

https://p.dw.com/p/4RkFF

በዛሬው የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች መሰናዶያችን በቴክዋንዶ ስፖርት በተለይም ጥሩ ብቃት እያሳዩ እና ተስፋም እያስጨበጡ ነው ከተባለላቸው አራት ሴት ታዳጊዎች ጋር ቆይታ አድርገናል።

ታዳጊዎቹ የአካዳሚው የአራተኛ ዓመት ተማሪ የ18 ዓመቷ አሚና ጀማል፣ የ17 ዓመት ታዳጊ ሙሉዕድል ግርማ፣ የ18 ዓመት ታዳጊ ሀይማኖት ደምሴ እና የ15 ዓመት ተስፈኛ ታዳጊ ፍቅር ደረጀ ናቸው፡፡ ታዳጊዎቹ ከተለያዩ የአገሪቱ አከባቢዎች ተመልምለው በብቃታቸው ተፈትነው ይህን ማዕከል የተቀላቀሉ ሲሆን፤ በዚህ እድሜያቸው በስፖርቱ ከተለያዩ የቀበቶ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ዳን ማእረግም የደረሱ ናቸው፡፡

እነዚህ ታዳጊ ሴቶች በስፖርቱ ተሳክቶላቸው እስከ ኦሎምፒክ መድረክ የአገራቸውን ባንድራ ስለማውለብለብም ያልማሉ፡፡ #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘገባ፡ ሱመያ ሳሙኤል

ቪዲዮ፡ ሥዩም ጌቱ