1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፓሪስ ለጨረታ ሊቀርብ የነበረዉ የኢትዮጵያ ሥዕል

ሐሙስ፣ ሐምሌ 17 2006

ኢትዮጵያ የበርካታ ባህልና የታሪክ ቅርሶች መገኛ ብትሆንም በአንፃሩ በተለያዩ መንገዶች ቅርሶቿ ከሀገር የሚወጡባቸዉ አጋጣሚዎች ብዙ ናቸዉ። እርግጥ ነዉ አንዳንድ ከሀገር የሚወጡ ቅርሶችን የማስመለስ እንቅስቃሴ አልፎ አልፎ ቢታይም አሁንም በርካታ የኢትዮጵያ ቅርሶች በተለያዩ ሃገራት ቤተ መዘክሮችና ግለሰቦች እጅ ላይ መገኘታቸዉ አልቀረም።

https://p.dw.com/p/1CiUX
Lalibela - Orthodoxe Christen
ምስል Reuters/Goran Tomasevic

ከእነዚህ አንዱ ሰሞኑን ፓሪስ ፈረንሳይ በሚገኝ «ሜዞን ፒያሳ» በተሰኘ ጥንታዊ የጥበብ ዉጤቶች መሸጫ ማጫረቻ ቤት ሊቀርብ የነበረዉ ጎንደር ከሚገኝ አባ እንጦንስ ቤተ ክርስቲያን እንደተወሰደ የሚነገርለት ሥዕል ነዉ። በ17ኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን የተሳለዉ የቅዱስ ዮሐንስ ታዋቂ ሥዕል ፓሪስ በአንድ ቤተ መዘክር እንዲቀመጥ ቢደረግም ከዚያም ከጠፋ ረዥም ጊዜ አስቆጥሯል። እናም ለጨረታ ከመቅረቡ በፊት የሥዕሉ ባለቤት ነኝ ያለዉ ቤተ መዘክር እንዳይቀርብ አግዶታል። ከጠፋ ከረዥም ጊዜያት በኋላ ለጨረታ ሊቀርብ የነበረዉ ኢትዮጵያዊዉ የጥበብ ሥራ እንዴትና በምን ወደፈረንሳይ ምድር መጣ? ከነበረበትስ ቤተ መዘክር እንዴት ሊጠፋ ቻለ? የወደፊት እጣ ፈንታዉስ የሚሉትን ጥያቁዎች ያነሳችዉ የፓርስ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ የሚመለከታቸዉን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ ልካልናለች።

ሃይማኖት ጥሩነት

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ