1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመኖች የባህል ትስስር ከ 25 ዓመት ዉሕደት በኋላ

ሐሙስ፣ ኅዳር 4 2007

በቀድሞዋ ምሥራቅ ጀርመን ይኖሩ የነበሩትና የዚያን ግዜዎቹ ኢትዮጵያዉያን የከፍተኛ ተቋም ተማሪዎች የሁለቱን ጀርመኖች ዉሕደት እንዴት አገኙት። የቀድሞቆቹ ተማሪዎች የዛሪዋን ጀርመንና ከዉሕደቱ በፊት የዛሬ 25 ዓመቱን የምሥራቅ ጀርመን የባህልና ኑሮ ልዩነት እንዲሁም ትስስር እንዲያጫዉቱን ጋብዘናል።

https://p.dw.com/p/1DmRy
Berlin Feierlichkeiten 25 Jahre Mauerfall Ballons Gorbatschow
ምስል REUTERS/F. Bensch

በርሊን ዉስጥ በጎርጎረሳዉያኑ ሕዳር 9/ 1989 ዓ,ም የተካሄደዉ ክስተት ጀርመናዉያን በዉቡ የታሪክ ማኅደራቸዉ የሚያስቀምጡት፤ አስደሳቹ እና በምሳሌነት የሚያቀርቡት ታሪካቸዉ ነዉ። ባለፈዉ ሳምንት በርሊን ላይ በድምቀት የተከበረዉ የበርሊን ግንብ የተናደበት 25ኛ ዓመት በዓል፤ በፖለቲካዉ መድረክ ጀርመኖች ለዓለም ምሳሌ የሆኑበት መሆኑ ይታወቃል። ለትምሕርት ጀርመን በመጡበት የግንቡን መፍረስና በዉጤቱም የምሥራቅና የምዕራብ ጀርመኖችን ዉሕደት በቅርብ የተከታተሉ ኢትዮጵያዉያንም ይህንን ይመሰክራሉ። በዚያን ግዜ በምስራቅ ክፍል ይኖሩ የነበሩ ተማሪዎች ዛሬ ስለ ዉሕደትና፤ በዉሕደት አንዳንድ የባህል፤ የአኗኗር ዘይቤ ሁሉ መቀየሩን ይመሰክራሉ። በዕለቱ ዝግጅታችን በምስራቃዊዉ ጀርመን ሲኖሩ 33ኛ ዓመታቸዉን የያዙትና በቀድሞዋ ምስራቅ ጀርመን የጋዜጠኝነት ትምህርትን ተከታትለዉ የዶክትሪት ማዕረግን ያገኙት አቶ መኮንን ሽፈራዉ እንዲሁም በጀርመን ሲኖሩ 30 ዓመት የሆናቸዉና፤ በምስራቅ ጀርመን በፋይናንስ፣ ኢኮኖሚክስና በንግድ አስተዳደር ማስተርስ ማዕረግን ይዘዉ በአሁኑ ወቅት በአንድ ድርጅት ውስጥ የሽያጭ ክፍል ሃላፊ ሆነዉ የሚያገለግሉትንአቶ መስፍን አማረን በእንግድነት ጋብዘናል። ዶክተር መኮንን ሽፈራዉ የዉጭ ሀገር ዜጎችና ጀርመናዉያን በባህልና በየዕለት ኑሮ ተጣምረዉ እንዲኖሩ ባደረጉት አስተዋዖ ከጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት ቢሮ በቅርቡ የክብር ሜዳልያን መሸለማቸዉን ይታወሳል። የሁለቱን ጀርመኖች ደስታ ለመካፈል ለማየት በቅተናል ያሉን ሁለቱ የቀድሞ የምስራቅ ጀርመን የከፍተኛ ተቋም ተማሪዎች ፤ በምስራቅና በምዕራብ ጀርመን መካከል የኑሮዉን የባህሉንአያያዝና ሁኔታን አጫዉተዉናል።

Berlin Feierlichkeiten 25 Jahre Mauerfall
ምስል picture-alliance/dpa/Rainer Jensen


ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ የበርሊን ግንብ የተገረሰሰበትን 25ኛ ዓመት በድምቀት ሲከበር ወደ ሁለት ሚሊዮን ህዝብ የግንብ አጥሩ ቆሞ በነበረበት ቦታ ዝግጅቱን ለመካፈል በርሊን ከተማ ላይ መገኘቱ ተመልክቶአል። የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል፤የተለያዩ የሃገሪቱ ፖለቲከኞችና የጀርመን ታዋቂ ሰዎች በዝግጅቱ ላይ ንግግር በማድረግ ደስታቸዉንም ገልፀዋል፤ ግዙፍ የሙዚቃ ድግስም ታይቶአል። ለዚህ ግንብ መፍረስ ትልቅ አስተዋፅዖን ያበረከቱት የቀድሞዉ የሶቭየት ሕብረት መሪ ሚሃኤል ጎርባቾቭ በርሊን ላይ በተዘጋጀዉ ድግሥ ላይ ዋንኛዉ ተጋባዥ እንግዳም ነበሩ። ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ