1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመንና ኩርዳውያንና የማስታጠቁ ጥያቄ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 15 2006

ኢራቅ ውስጥ አክራሪ እስላማዊ ኃይል የተሰኘውን ፣ (IS) በሚል ምህጻረ ቃል የታወቀውን የሱኒዎች ታጣቂ ኃይል ለመመከት ፤ የሰሜን ኢራቅ ራስ ገዝ መስተዳድር፣ ኩርዲስታን ፣ ምን ዓይነት የጦር መሣሪያ ያስፈልገዋል? ከጀርመን ፌደራል ሪፓብሊክ

https://p.dw.com/p/1Cywb
ምስል Reuters

የተጠየቀውና ያስፈልጋል የተባለው ጦር መሣሪያ ዓይነት በማከራከር ላይ የሚገኝና ውስብስብ ሁኔታዎችን ያስከተለ መሆኑም እየተነገረ ነው። የሚንስትሮች ም/ቤት ለኩርዲስታን በቀጥታ ጦር መሣሪያ እንዲቀርብ መወሰኑን ትናንት ቢያሳውቅም በጀርመን የሕዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት (ቡንደስታኽ) የተቃውሞው ወገን ፣ ፓርላማውም አብሮ የመወሰን መብት ሊኖረው ይገባል በማለት ወጥሮ ይዟል።

ጀርመን ፤ ለኩርዲስታን ጦር መሣሪያ ስለምታቀርብበት ሁኔታ የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት (ቡንደስታኽ) ክርክሩን ቀጥሏል። በዚያው በቡንደስታኽ፣ የክርስቲያን ዴሞክራት ሕብረትና ክርስቲያን ሶሺያል ሕብረት የሕዝብ እንደራሴዎች ተጠሪ ፊሊፕ ሚስፌልደር፤ ለአንዲህ ዓይነቱ ውሳኔ የፓርላማ አብሮ የመወሰን ጥያቄ ሊነሣ አይችልም ባይ ናቸው።

Pressekonferenz von der Leyen Steinmeier zu Waffenlieferungen an irakische Kurden
ምስል Odd Anderson/AFP/Getty Images

«እንደሚመስለኝ፤ ጉዳዩን በጥሞና በመመርመር ረገድ ከባድ ሁኔታ ቢያጋጥምም ውሳኔው ትክክል ነው። ህጋዊ የሆነ ለየት ያለ ሁኔታ ሲያጋጥም ተመሳሳይ ምላሽ የሚሰጠበት ደንብም አለ። ይህ ደግሞ ጠቃሚ ጉዳይ ነው። የጦር መሣሪያ አቅርቦትን በተመለከተ ፣ ይህ በእርግጥ የአቋምም ሆነ የመርሕ ለውጥ ነው። ይሁንና ትክክለኛ ውሳኔ ነው ብዬ ነው የማምነው።»

እ ጎ አ በ 1970ኛዎቹ ዓመታት በ ጀርመን ሀገር ትምህርታቸውን በመከታተል፣ በኢንጂኔሪንግ የዶክተርነት ማዕረግ ያገኙት የኢራቅ ምክትል ጠ/ሚንስትር ሮውሽ ሻዌስ፣ የኩርዳውያን ወኪል ሲሆኑ፤ ዛሬ በኤርቢልና ሞሱል መካከል በጦሩ ግንባር በመገኘት ይህን ነበረ ያሉት።

«አሸባሪዎቹን፣ እንደምንም አሁን እኔ ከምገኝበት አካባቢ ዝር እንዳይሉ ልናቆማቸው እንችላለን። የመከላከያውን ግንባርም አጠናክረን ፤ በአቅዳችን መሠረት በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን።

በመሠረቱ፤ ከልብ እንደማምነው አሸባሪዎቹ ወደ ቁንዱስ ለመምጣት ምንም ዓይነትv ዕድል የላቸውም እንዲያውም ባጠቃላይ በኢራቅ የመቆየት ተሳፋውም ዕድሉም የላቸውም። ውሳኔው በኛ እጅ ነው። የኢራቅ የፖለቲካ መርሕ የሚወስነው ጉዳይ ነው የሚሆነው። ምን ያህል ጊዜ እየተዋጉ ይቆያሉ? እኛ ነን ጉዳዩን ፈር የምናስይዘው።»

ሮውሽ ሻዌስ፣ የጀርመን ጦር መሣሪያ ቢደርሰን በጥንቃቄ ስለምንይዘው በምንም ዓይነት ከደፈጣ ተዋጊዎች በተለይ ተባባሪዎች ከሚባሉት PKK እጅ አይገባም ነው ያሉት።

Symbolbild Deutschland Waffenexporte
ምስል Getty Images

«ከ PKK ጋር ቀጥተኛ ግንኙነትም የለንም። አንዳንድ ቦታዎች አሉ ፤ የ PKK ምሽጎች ወይም የስደተኞች መጠለያዎች! በውጊያው አብረው ለመሳተፍ ይሻሉ። ግን የእነርሱ ተሳትፎ ያን ያህል ትርጉም የሚኖረው አይደለም። ሁለተኛ ፤ የኩርዲስታን መስተዳድር፤ በኢራቅ ሕገ መንግሥት ዕውቅና የተሰጠው ነው። ከውጭ ው ዓለም ጋር ግንኙነት ያለውና በአሸባሪዎች ያለው አቋምም በሚገባ የታወቀ ነው።»

ፊሊፕ ሚስፌልደር አጠራጣሪ መስሎ ስለታየው ስለሁለቱ ወገኖች የጦር ትብብርና የጀርመን ጦር መሣሪያም ከPKK ደፈጣ ተዋጊዎች እጅ አይገባም ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥቄ ተከታዩን ምላሽ ነው የሰጡት---

«ባለፈው ሳምንት ራሴ በኩርዲስታን ራስ ገዝ መስተዳድር ርእሰ ከተማ ፤ኤርቢል ነበርሁ። እናም በኩርዲስታንና በ PKK መካከል ያለው ግንኙነት ያን ያህል የወደጅነት ነው የሚያሰኝ አይደለም። የ PKK ደፈጣ ተዋጊዎችም በዚሁ መሣሪያ ካልታጠቅን የሚሉ አይደሉም ፤ ውሎ አድሮ፣ የራሳቸውን ጥቅም የሚጎዳ ነገር እንዲፈጸም አይሹምና!»

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ