1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን-ኢትዮጵያውያን ወጣቶች እና ዓመት በዓል

ዓርብ፣ መስከረም 2 2007

ለሌሎቹ የአዘቦት ቀን በሆነበት የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት ዕለት ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በዓሉን እንዴት አከበሩት? ባህልን በማስተዋወቁ ረገድስ ምን ያህል ዝግጁ ናቸው?

https://p.dw.com/p/1DAfz
amharisch alphabet
ምስል DW/Azeb Tadesse Hahn

አነሰም በዛም ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የትናንትናውን መስከረም አንድ ቀን ፤ መልካም አዲስ አመት እየተባባሉ አሳልፈውታል።እዚህ ጀርመን የትናንትናው ቀን አስቦ የዋለው ደጀኔ ለገሰ የበርሊን ከተማ ነዋሪ ነው። ለዶክትሬት ትምህርት ወደ ጀርመን ከመጣ አራት ዓመታት ተቆጠሩ። በዓሉ ሐሙስ ዕለት በመዋሉ አስቦት ቢውልም ፤ ቅዳሜ ከጓደኞቹ ጋር ተሰብስቦ ለማክበር ተነስቷል።

ጀርመን ሀገር ተወልዳ ያደገችው ኢትዮ ጀርመናዊት ቤዛ ሀን፤ ስለ ኢትዮጵያውያን አዲስ አመት የምታውቀው ከቤተሰብ እና ጓደኞቿ ከሰማችው ቢሆንም በቅርብ ለምታውቃቸው ዘመዶቿ እና ጀርመናዊ ጓደኞቿ እንኳን አደረሳችሁ ብላለች።

ሌላው አዲስ አመቱን መነሻ በማድረግ ለዛሬ ያነጋገርነው የኮሎኝ ከተማ ነዋሪ የሆነው እስጢፋኖስ ሳሙኤልን ነው።ልክ እንደ ደጀኔ እስጢፋኖስም ስለ አውደ ዓመት ሲያስብ ትዝ የሚለው ቤተሰቡ እና የተጋበዙ እንግዶችን መጠበቅ ነው።ከዚህም ሌላ እስጢፋኖስን የኢትዮጵያ አዲስ ዓመትን መነሻ አድርጎ አንድ ፕሮግራም አዘጋጅቷል። ሁሉንም ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ