1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዶይቸ ቬለ እና የአሜሪካ አድማጮቹ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 20 2007

የጀርመን ድምፅ ራድዮ፣ ዶይቸ ቬለ በአሜሪካ የሚኖሩት አድማጩች ስርጭቱን በስልክ የሚያደምጥበት አገልግሎት መጀመሩ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱ ተገለጸ። ይህንኑ አገልግሎት ተግባራዊ ያደረገው በዩኤስ አሜሪካ የሚገኘው «አውዲዮ ናው » የተሰኘው ድርጅት የራድዮ ስርጭት በስልክ የማድመጡ አገልግሎት

https://p.dw.com/p/1Debv
Deutsche Welle Bonn Französisch Sendestudio SK2
ምስል DW/A. Le Touzé

አሜሪካ ውስጥ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በጣም የተለመደ እና ተወዳጅ መሆኑን አስታውቋል። በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የሚኖሩት ኢትዮጵያውያንም ይኸው አዲስ የዶይቸ ቬለ አገልግሎት ስርጭቱን በፈለጉበት ሰዓት እና ቦታ ለማድመጥ የተመቻቸ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል። አድማጮች ከፊታችን እሁድ፣ እአአ ከህዳር ሁለት፣ 2014 ዓም በኋላ፣ የሰዓት ለውጥ ስለሚደረግ፣ ይህንኑ የ«አውዲዮ ናው » አገልግሎት በምሥራቃዊ የዩኤስ አሜሪክ የሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ አምስት ሰዓት ወይም 11 a.m. ማግኘት እንደምትችሉ ለመግለጽ እንፈልጋለን።

አበበ ፈለቀ

አርያም ተክሌ

ተክሌ የኋላ