1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፕሬዚዳንት ኦባማ እና የጠ/ሚ ኃይለማርያም ዉይይት

ዓርብ፣ መስከረም 16 2007

የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በሁለቱ ሀገራት ዙርያ ዉይይት አደረጉ። የሁለቱ መንግሥታት መሪዎች ትናንት ኒዮርክ ላይ ዉይይት ከማድረጋቸዉ በፊት በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤

https://p.dw.com/p/1DLjE
Obama Koalition gegen IS 23.09.2014 New York
ምስል Reuters/Kevin Lamarque

የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በንግድ፤ በኤኮኖሚ እና በደሕንነት ዘርፎች የበለጠ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ጋር በአሁኑ ጊዜ ዉይይት ማካሄዳቸው በሶርያ ከጀመሩት ዘመቻቸዉ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል አንድ የአሜሪካ የአፍሪቃ ፖሊሲ ጉዳዮች ተንታኝ ይናገራሉ። ዝርዝሩን የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ልኮልናል።

አበበ ፈለቀ
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ