1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጤፍ መታወቅ አደጋ ወይስ ገጸበረከት?

እሑድ፣ የካቲት 15 2007

ኢትዮጵያ በጤፍ መገኛነቷ ብቻ ሳይሆን እንደ እህል ለምግብነት በመጠቀሟም የምትጠቀስ ብቸኛ ቀዳሚ ሀገር ናት። ጤፍን ከተራ የዱር ተክልነት ወደምግብነት በመለወጥ የኢትዮጵያ ገበሬ ግንባር ቀደም ተጠቃሚ መሆኑን የእጸዋት እና እህል ዘር ተመራማሪዎች ያረጋገጡት እዉነት ነዉ።

https://p.dw.com/p/1Ef19
24112006 PZ TEFF.jpg
ምስል DW-TV

በኢትዮጵያ የብዝሃ ሕይወት ተቋም ወደ6000 የሚጠጉ የተለያዩ የጤፍ ናሙናዎች በዘረመል ባንክ ተጠብቀዉ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ገበሬ የጤፍ ዘርን ተፈጥሯዊነቱን በጠበቀ መንገድ በባህላዊ ዘዴ እያመረተዉ ለዘመናት ሲጠቀምበት ቆይቷል። ጤፍ ዛሬ የኢትዮጵያ ብቻ ምግብ መሆኑ እየተለወጠ የመጣበት ሁኔታ ይታያል። በዉስጡ ባለዉ ለጤና ተስማሚ ንጥረነገርና ተፈጥሮ ምክንያት ሌላዉ ዓለም በተለይም አዉሮጳና አሜሪካ ጤፍን በስሙ ጤፍ ብለዉ እየጠሩ ምግብነቱን እያስተዋወቁና እያመረተቱትም እየተጠቀሙበትም ይገኛሉ። ጤፍ የምርምርና የገንዘብ አቅም ያላቸዉን የሌሎችን ወገኖች ቀልብ መሳቡ ለሕልዉናዉ አደጋ ወይስ ገጸ በረከት? የጤፍ ዘርስ የባለቤትነትና ተጠቃሚነት ድርሻዉ? ዶቼ ቬለ በዚህ ሳምንት ሶስት የእጽዋት ምርምር ባለሙያዎችን በመጋበዝ ለጤፍ ሊደረግ ስለሚገባዉ ክብካቤና ጥንቃቄ፤ የባለቤትነት መብትና ጥበቃዉ አወያይቷል። ሙሉዉን ዉይይት ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ