1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የገንዘብ ዋጋ መቀነስ

እሑድ፣ ነሐሴ 4 2006

የአንድ ሀገር መገበያያ ገንዘብ በተለያዩ ምክንያቶች ዋጋዉ ወይም የመግዛት አቅሙ የሚቀንስበት አጋጣሚ በርካታ ነዉ። በተለይ ደግሞ ጠንካራ ከሚባሉት ዓለም አቀፍ መገበያያ ገንዘቦች ጋ ሲወዳደር እያደር አቅሙ ዝቅ የሚልበት አጋጣሚ ነው ያለው ።

https://p.dw.com/p/1Crea
Symbolbild Bezahlung Kasse Geld
ምስል Fotolia/StefanieB.

የዉጭ ምንዛሪ ፍላጎት ከፍ በሚልበት አጋጣሚ ደግሞ ይህ ጎልቶ ይታያል። የኤኮኖሚ ባለሙያዎች ይህን የፍላጎትና አቅርቦት ያለመመጣጠን ዉጤት ነዉ ይሉታል። ኢትዮጵያ ዉስጥ የአንድ ዶለር ምንዛሪ ከ2 ብር ከ40 ሣንቲም ተነስቶ፤ ባለፉት ዓመታት ከፍ እያለ ሄዶ አሁን 19 ብርን አልፏል። ኢትዮጵያ የምንዛሪ መጠኑን ከፍ ማድረጓን ብትቀጥል የብር የመግዛት አቅም እንዴት ሊሆን ይችላል? አንድ ሀገር መገበያያ ገንዘቡ ዋጋዉን ጠብቆ ለመዝለቅስ ምን ማሟላት ይጠበቅበታል? የዶቼ ቬለ የዚህ ሳምንት የዉይይት ርዕሰ ጉዳይ ነዉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ