1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የፖሊስ ጣቢያ ቆይታ

ረቡዕ፣ መስከረም 15 2006

አቶ ትዕግሥቱ አወሉ፣ የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዛሬ ከምሽቱ 12 ሰዓት ግድም ለዶቼ ቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት ቃለ መጠይቁ እስከተደረገበት ሰዓት ድረስ ዶክተር ነጋሶና አንድ የፓርቲውን ቅስቀሳ ይቀርፅ የነበረ ካሜራ ማን፣ በጉለሌ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ ነበሩ ።

https://p.dw.com/p/19oaQ
ምስል DW

የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ የሚገኘው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ፣ ዛሬ ከቀትር በኋላ፣ ከ8 ሰዓት አንስቶ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንዲቆዩ መደረጉን አንድ የፓርቲው፣ ባለሥልጣን አስታወቁ ። አቶ ትዕግሥቱ አወሉ፣ የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዛሬ ከምሽቱ 12 ሰዓት ግድም ለዶቼ ቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት ቃለ መጠይቁ እስከተደረገበት ሰዓት ድረስ ዶክተር ነጋሶና አንድ የፓርቲውን ቅስቀሳ ይቀርፅ የነበረ ካሜራ ማን፣ በጉለሌ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ ነበሩ ። ዶክተር ነጋሶና በዋስ የተለቀቀው ካሜራማን ከፖሊስ ጣቢያው መመለሳቸውን አቶ ትዕግሥቱ ሥርጭታችን ካበቃ በኋላ ገልፀውልናል ። ዛሬ ከሰዓት በኋላ ስለሆነው እንዲያስረዱን አቶ ትዕግሥቱ በስልክ ጠይቀናቸዋል ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ