1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩክሬን ቀዉስ የአሜሪካ ምላሽ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 10 2006

የሩሲያን ጨምሮ የዩክሬን የዩናይትድ ስቴትስና የአዉሮጳ ኅብረት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ጄኔቭ ላይ ትናንት ባካሄዱት ዉይይት አማካኝነት የደረሱበት መግባባት በቀዉስ በተወጠረችዉ ሀገር የተባባሰዉን ሁኔታ ለማርገብ ያስችላል እየተባለ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1Bkq5
Ukraine Krise Außenminister Gespräch 17.04.2014 Genf
ምስል Reuters

ታጣቂ ኃይሎች ነፍጣቸዉን እንዲያስቀምጡ፤ በኃይል የተያዙ የመንግስት ሕንፃዎችንም እንዲለቁ፤ ጎዳናዎች ላይ የሚታዩ ሥርዓት ያጡ ግጭት ቀስቃሽ እንቅስቃሴዎችም እንዲገቱ ሩሲያ ድምጿን አሰምታለች። በጄኔቭ የተደረሰዉ ዲፕሎማሲያዊ ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ሩሲያ ጉልህ ሚና መጫወት እንደሚጠበቅባት ዩናይትድ ስቴትስ አመልክታለች። የዩክሬንን ዉጥረት ለማርገብ ሩሲያ ካልተባበረች ደግሞ ተጨማሪ ኪሳራ ሊደርስባት እንደሚችል ነዉ አሜሪካ ያስጠነቀቀችዉ። ወታደራዊ ርምጃ ግን በአሜሪካ በኩል በአማራጭነት አለመያዙን ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ገልጸዋል። የዩክሬንን ቀዉስና የጄኔቫዉን ጉባኤ አስመልክቶ አሜሪካ የሰጠችዉን ምላሽ የዋሽንግተኑ ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ እንደሚከተለዉ አጠናቅሮ ልኮልናል።

አበበ ፈለቀ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ