1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የየመን ወቅታዊ ሁኔታና ኢትዮጵያውያን

ረቡዕ፣ መጋቢት 23 2007

በሣዑዲ ዐረቢያ መራሹ የአየር ጥቃት የመን ውስጥ የተከፈተው ዘመቻ ስድስተኛ ቀኑን አስቆጥሯል ። በየመን የስደተኞች መጠለያ ከ40 በላይ ስደተኞች የተገደሉበትና 65 የቆሰሉበት የሰኞው የአየር ጥቃት ማነጋገሩ ቀጥሏል ። የየመኑ ወኪላችን ከዓለም ዓቀፍ የስደተኞች ድርጅት IOM አገኘሁት ባለው መረጃ ከሟቾቹ መካከል ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል ።

https://p.dw.com/p/1F0HI
Kämpfe im Jemen
ምስል Reuters/N. Rahma

ቁስለኞቹ ሀረድ በሚባል ቦታ አንድ ሐኪም ቤት እንደሚገኙም የየመኑ ወኪላችን ጠቅሷል። በሣዑዲ ዐረቢያ አዝማችነት በአየር የተከፈተው ጥቃት ዛሬ የአማጺያኑን ሚሳይሎችን እና የጦር መሣሪያ ማከማቻ መጋዘኖችን እንዳወደመ፣ ማስራቅ በተባለው ቦታ 40 በላይ ስደተኞች መገደላቸውን ደግሞ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። የተገደሉት ሰዎች የየትኛው ሀገር ዜጎች እንደሆኑ ግን የዜና ምንጮቹ አልጠቀሱም አልጠቀሱም። የየመኑ ወኪላችን ግሩም ተክለሐይማኖትን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬው ነበር። በየመን ዛሬ ጦርነቱ ምን መልክ እንዳለው በመግለጥ ይጀምራል።

ግሩም ተክለሃይማኖት

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ