1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የየመኑ ጦርነትና ኢትዮጵያዉን ስደተኞች

ረቡዕ፣ መጋቢት 23 2007

ባለፈዉ ሰኞ ከአዉሮፕላን የተጣለ ቦምብ መዝራቅ በተሰኘዉ መጠለያ ጣቢያ የተጠለሉ አርባ ስደተኞች ወይም ተፈናቃዮችን መግደሉ፤ ጦርነቱ ከተሳታፊዎቹ አልፎ የስደተኞችን ሕወት እያስገበረ መሆንኑ አረጋጧል።በጥቃቱ ከተገደሉት በተጨማሪ ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች ቆስለዋል።ከሟች ቁስለኞቹ መካካል ኢትዮጵያዉን እንደሚገኙበት አንዳድ ዘገቦች ጠቁመዉ ነበር።

https://p.dw.com/p/1F1Bz
ምስል Reuters/Abdullah

የኢትዮጵያ መንግሥት በየመኑ ጦርነት ለአደጋ የተጋለጡ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን ለመርዳት እየጣረ መሆኑን አስታወቀ።ሳዑዲ አረቢያ የምትመራዉ የዓረብ ሐገራት ጦር የመንን መደብደብ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያዉንን ጨምሮ የመን የሚኖሩ የዉጪ ሐገር ስደተኞች ለእስጊ አደጋ ተጋልጠዋል።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር እንዳስታወቀዉ ለአደጋ የተጋለጡ ስደተኞችን አንድም ከየመን ለማዉጣት አለያም ባሉበት ለመርዳት በየመን የኢትዮጵያ መልዕክተኞች ስደተኞቹን እየመዘገቡ ነዉ።ሥደተኞቹ ከዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ጋር የሚገናኙበት የሥልክ መስመርም አዘጋጅቷል።

Jemen Abdel Malek al-Huthi Anführer Huthi Rebellen
ምስል picture-alliance/epa/Y. Arhab

የመን ሠላም ከራቃት በርግጥ ዓመታት ተቆጥረዋል።የመን የሚኖሩ ወይም ወደ ሐብታሞቹ የፋርስ ባሕረ-ሠላጤ አካባቢ ሐገራት ለመጓዝ የመን የገቡ ኢትዮጵያዉን ስደተኞችም በተደጋጋሚ እንደሚሉት ከስደተኝነትም አልፎ የሰዉነት ክብርና ወግ አይተዉ አያዉቁም።ሳዑዲ አረቢያ የምትመራዉ የአረብ ሐገራት ጦር የሁቲ ሚሊሻዎችን ይዞታ መደብደብ ከጀመረ ጀምሮ ደግሞ አስከፊዉ የስደተኞች ኑሮ በመኖር-አለመኖር መሐል ተቃርጧል።

Flüchtlinge Boot Symbolbild Jemen Äthiopien
ምስል picture-alliance/dpa/Xinhua /Landov

ባለፈዉ ሰኞ ከአዉሮፕላን የተጣለ ቦምብ መዝራቅ በተሰኘዉ መጠለያ ጣቢያ የተጠለሉ አርባ ስደተኞች ወይም ተፈናቃዮችን መግደሉ፤ ጦርነቱ ከተሳታፊዎቹ አልፎ የስደተኞችን ሕወት እያስገበረ መሆንኑ አረጋግጧል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዳስታወቀዉ በጥቃቱ ከተገደሉት በተጨማሪ ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች ቆስለዋል።ከሟች ቁስለኞቹ መካካል ኢትዮጵያዉን እንደሚገኙበት አንዳድ ዘገቦች ጠቁመዉ ነበር።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ እንደሚሉት ግን ኢትዮጵዉያን ለመጎዳታቸዉ መንግሥታቸዉ ምንም ማረጋጋጪያ አላገኘም።

ኢትዮጵያዉያኑ ስደተኞች በሰኞዉ ጥቃት ተጎዱም አልተጎዱ ከሞት፤ መቁሰልና ከሌላ አደጋ ጋር እንደተፋጠጡ ነዉ።ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ቴዎድሮስ አድሐኖም ኢትዮጵያዉኑ ስደተኞች እርዳታ የሚጠይቁባቸዉን ሥልኮች በማበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አሰራጭተዋል።ቃል አቀባይ ተወልደ ምዝገባም ተጀምሯል ይላሉ።

የመን ዉስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉን ስደተኞች ቁጥር አቶ ተወልደ እንዳሉት በዉል አይታወቅም።አንዳድ ምንጮች ከሰባ እስከ መቶ ሺሕ ሲያደርሷቸዉ አቶ ተወልደ በአስር ሺዎች ብለዉ ማለፉን ነዉ-የመረጡት።አሁን የሚመዘገቡት ስደተኞች እንደየፍላጎታቸዉ ወደ ሐገር ይመለሳሉ።አቶ ተወልደ ይቀጥላሉ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ስደተኞቹን ለመርዳት በተለይም ወደ ሐገራቸዉ ለማጓጓዝ ከዚሕ ቀደም እንደሚያደርገዉ ሁሉ IOMን ከመሳሰሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች ጋር ተባብሮ እየሠራ መሆኑንም አቶ ተወልደ አሰታዉቀዋል።

ይሁንና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እስካሁን የመን ዉስጥ በተለያዩ መስሪያ ቤቶቹ ይሠሩ የነበሩ የዉጪ ሐገር ዜጎችን በመሉ ከየመን አስወጥቷል።ድብደባዉ ግን አላባራም።

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ 

 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ