1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዛምቢያ ሀምሳ የነፃነት ዓመታት

ቅዳሜ፣ ጥቅምት 15 2007

ዛምቢያ ከብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ ከተላቀቀች ትናንት፡ እአአ ጥቅምት ሀያ አራት፡ 2014 ዓም ሀምሳ ዓመት ሆናት። የነፃነቱ ዓወዳመት ትናንት በመላ ዛምቢያ በይፋ የተከበረ ሲሆን፡ የሀገሪቱ ዜጎች ዕለቱን በዚህ በያዝነው የጥቅምት ወር በተለያዩ ዝግጅቶች በማክበር ላይ ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/1Dc9v
Viktoria-Fälle in Sambia und Simbabwe
የቪክቶርያ ሃይቅ ፏፏቴምስል imago/Xinhua

ውዝግብ በበዛበት አካባቢ የምትገኘው ዛምቢያ ባለፉት ሀምሳ የነፃነት ዓመታት መረጋጋት የሰፈነባት ሀገር ለመሆን ከመብቃትዋ ጎን፣ የሚሞገስ የፖለቲካ ተሀድሶ በማድረግ ሥርዓተ ዴሞክራሲን ማስተዋወቅ ተሳክቶላታል፥ ኤኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዕድገትም አስመዝግባለች። ያም ቢሆን ግን፡ ከሕዝቧ መካከል ሰባ ከመቶው አሁንም በካው ድህነት ውስጥ ነው የሚገኘው።

አርያም ተክሌ
ልደት አበበ