1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወጣቶች ዓለም አቀፍ የሳይንስና ኢንጂኔሪንግ ውድድር

ረቡዕ፣ ግንቦት 12 2007

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ፣ ገና ኮሌጅ ባልገቡ ወጣቶች ዘንድ በያመቱ የሚካሄድ ዓለም አቀፍ የሳይንስና ኢንጂኔሪንግ ምርምር ውድድር አለ። The International Science and Engineering Fair የሚባል! የዘንድሮው፤ ከግንቦት 2-7

https://p.dw.com/p/1FTNo
ምስል picture-alliance/dpa

የወጣቶች ዓለም አቀፍ የሳይንስና ኢንጂነሪግ ዉድድር

,2007 ዓ ም ፣ በ ፒትስበርግ ፣ ፔንስልቬንያ ነበረ የተካሄደው ። ከ 70 ሃገራት የተውጣጡ ከ 1700 በላይ ወጣት ተማራማሪዎች ተሳትፈውበታል። ጀርመናውያኑ ቀንቷቸው ሽልማት- በሽልማት ሆነዋል። ዋና ጽ/ቤቱ በሐምበርግ የሚገኘው ዘንድሮ 50 ዓመት የሚሆነው «ዩገንድ ፎርሽት» (ወጣቱ ይመራመራል ) የተባለው ድርጅት የሚያወዳድራቸው የጀርመን ወጣቶች፣ ከመደበኛ ትምህርታቸው ውጭ በለጋ ዕድሜ የሚያካሂዱትን የሳይንስና ሥነ ቴክኒክ የምርምር ተግባር ለመዳሰስ እንሞክራለን።

በዩናይትድ ስቴትስ ፤ እ ጎ አ በ 1950 የተቋቋመው ፤ «ሳይንስ ሰርቭስ » ይባል በነበረው ፣ እ ጎ አ ከ 1997 ዓ ም ወዲህም የሳይንስና የሕብረተሰብ ማሕበር ተብሎ ፣ «ኢንተል» በተሰኘ ኩባንያ ድጋፍ ፣ የሚንቀሳቀሰው ድርጅት፤ ለጀርመኑ «ዩገንድ ፎርሽት» አርአያ መሆኑ ነው የሚነገረው። እ ጎ አ ከ 2012 ወዲህ ብቻ፤ 7 የዚሁ ዓለም አቀፍ የሳይንስና ኢንጂኔሪንግ ዐውደ ርእይ ተሳታፊዎች የነበሩ፣ በኋላ የኖቤል ሽልማት ለማግኘት መብቃታቸውን ለመገንዘብ ተችሏል።

Bundessieger von Jugend forscht - Technik Der Bundessieger beim Wettbewerb Jugend forscht im Fachgebiet Technik, Florian Schnös aus Schweinfurt (Bayern)
ምስል picture-alliance/dpa

በያመቱ በሚዘጋጀው በጠቅላላ እስከ 4 ሚሊዮን ዶላር በሚመደብበት የ«ኢንተል ሳይንስና ኢንጂኔሪንግ ውድድር፣ 8 ሚሊዮን ያህል ተማሪዎች ናቸው የሚሳተፉት። ጀርመንን ወክለው ከዩገንድ ፎርሽትv ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የተጓዙት 15 ወጣቶች ሲሆኑ እነርሱም በአጠቃላይ 17 ሽልማቶችን ሰብስበዋል። ከሄሰን ፌደራል ክፍለ ሀገር ፣ ቦርከን ከተባለችው የካስል ከተማ መዳረሻ ፣ የ 18 ዓመቱ ወጣት፣ አርነ ሄንዘል፣ የ 17 ቱ ወጣት ኒክላስ ፋውት ፤ ከማርባሕ፤ ባደንቩርተምበርግ፣ ከ 24 ዓለም አቀፍ ወጣት ሳይንቲስቶች ጋር ተደምረዋል።

አርነ ሔንዘል፤ በሥነ ቅመማ በተደረገ ልዩ ውድድር የተመደበውን የአንደኛ ደረጃ ሽልማት --3,000 ዶላር እንዲሁም በተጨማሪ ውድድር በማሸነፍ ባጠቃላይ 7,500 ዶላር ለማግኘት በቅቷል። ኒክላስ ፋውት፤ የውስጥ አካል መመርመሪያ ለየት ያለ መሣሪያ በማቅረብ በአጠቃላይ የ 9,500 ዶላር ሽልማት ተቀብሏል። በ 3 ማዕዘናዊ ስዕል አታሚ መሣሪያ፤ በኢንጂኔሪግ፤ በፊዚክስና ሥነ-ፈለክ፤ ለተፈጥሮ አካባቢ የሚበጀ ነዳጅ በመቀመም፣ በኮምፒዩተር ሥዕል የማንቀሳቀስ ጥበብና በመሳሰለው እንግዲህ ባጠቃላይ 15 ጀርመናውያን ወጣቶች ናቸው ተሸላሚዎች ለመሆን የበቁት።

እነዚሁ ፣ ከተለያዩ የአገሪቱ ፌደራል ክፍለተ ሀገር የተውጣጡት ወጣት ጀርመናውያን ተመራማሪዎች፣ ለውድድር ተሰልፈው ባጭሩ ይህን መሰል ክብርና ሽልማት በማግኘታቸው፤ መሪው ተጠሪ ድርጅት Jugend Forscht ምን ተሰምቶት ይሆን?! በሐምበርግ ፤ የድርጅቱ ማዕከላዊ ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት ጉዳይ መሪና አስተባባሪ ሄር ዳንኤል ጊዘ እንዲህ ይላሉ---

«በአድናቆት ፤ በደስታ ነው ልባችን የተሞላው፤ እስከምናስታውሰው ድረስ አንድ የጀርመን ወጣት ተማራማሪዎች ቡድን፤ በዓለም አቀፍ ውድድር በተሳካ ሁኔታ በመደምደም ከዚህ ቀደም የአሁኑን ያህል ሽልማት ያገኘበት ጊዜ የለም። ከጀርመናውያን ወጣት ተመራማሪዎች፤ ጎን ለጎን፤ ዩ ኤስ አሜሪካ ውስጥ በጥንታዊው የወጣቶች የምርምር ድርጅት ውድድር ይካሄድ ነበረ። ለዚህም ነበረ የ«ዩገንድ ፎርሽት» (ወጣቱ ይመራመራል) መሥራች ፤ ጋዜጠኛ ሄንሪ ናነን፤ በጊዜያቸው (ከ 50 ዓመት በፊት መሆኑ ነው) በሉፍታንዛ ቡድናቸውን ይዘው ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በመጓዝ በውድድር ለመሳተፍ የቻሉት። በዩገንድ ፎርሽት ፍሬ ሐሳቡ ፤ ያኔ፤ ከአድማስ ማዶ ፣ ከድንበር ባሻገር በመመልከት ችሎታ፣ ተሰጥዖ ፣ ያላቸውን በተሣካ ሁኔታ የሚሳተፉ ብሔራዊ ወኪሎቻችን የሆኑትን ወጣቶች ከሌሎች ዓለም አቀፍ ወጣቶች ጋር ችሎታቸውን እንዲያመዛዝኑ ዕድል ለመስጠት ከሳይንሳዊ ሙያ ጋር ንፅፅር እንዲያደርጉ ብቻ ሳይሆን ግንኙነት በመመሥረት ከሌሎች አገሮች ተመራማሪ ወጣቶች ጋር የመተዋወቅ ዕድል እንዲያገኙማብቃት ነው። ለወደፊቱ፣ ሥምሪታቸው የሙያ በሮች ክፍት እንደሚሆኑላቸው ማመላከት ፣ በሌሎች አገሮች፤ ሕዝቡ ምን እንደሚያጓጓው ፤ ምን እንደሚያንቀሳቅሰው ምን እንደሚያሳስበው ለመገንዘብ ይበጃል።»

Jugend Forscht 2013 Bundessieger Mathematik Informatik
ምስል Stiftung Jugend forscht e. V.

በዩናይትድ ስቴትስ በተዘጋጀው 1,700 ያህል ወጣት የሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ተመራማሪዎች በተሳተፉበት ዓለም አቀፍ ውድድር ዋናውን ሽልማት ማለትም ለነጻ የትምህርት ዕድል የ 75,000 ዶላር ሥጦታ ያገኘው የሕዝብ ማመላለሻ አይሮፕላኖች ንፁህ አየር ማቅረቢያው ዘዴ ተሻሻሎ እንዲቀርብ ያደረገው፤ ሬይመንድ ዋንግ የተባለው የ 17 ዓመት ወጣት ካናዳዊ ነው። ወደ ተሣፋሪዎች ክፍል በዛ ያለ ንፁህ አየር እንዲገባ እንዲሁም ሳንክ የሚስከትለው እጅግ እንዲቀነስ በማስቻሉ ነው በአንደኛ ደረጃ የተመደበውን ሽልማት ያገኘው።

ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በመጓዝ፤ በዓለም አቀፉ ውድድር ሽልማት ለማግኘት የበቁት 15 ጀርመናውያን ወጣቶች ፣ አምና በጀርመኑ ብሔር አቀፍ የዩገንድ ፎርሽት ውድድር ለሽልማት የበቁ ናቸው። ዘንድሮ በአገር አቀፉ ውድድር የሚያሸንፉት በመጪው ዓመት በአሜሪካው ዓለም አቀፍ ውድድር ለመሳተፍ ዕድሉ ይጠብቃቸዋል።

ዩገንድ ፎርሽት፣ በራይንላድ ፋልትዝ ፌደራል ክፍለ ሀገር ፤ በራይን ወንዝ ዳር በምትገኘው ከተማ ፣ በሉድቪክስሐፈን ፣ BASF በሚል ምሕጻር ከሚታወቀው Badische Anilin- & Soda-Fabrik ከተሰኘው የሥነ ቅመማ ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኩባንያ ጋር በመተባበር፣ ከግንቦት 18-22 ,2007 50 ኛ ዓመቱን በድምቀት ለማክበር በዝግጅት ላይ ነው። ድርጅቱ ባለፉት 50 ዓመታት ፈጽምኩ የሚላቸው ዐበይት ጉዳዮች ምን ይሆኑ?---

«ዩገንድፎርሽትን፧ ይህን አወዳዳሪ ድርጅት ከሌሎች የተለዬ የሚያደርገው ዓርማውነው።የቀድሞው
የ«እሽተርን» መጽሔት ዋና አዘጋጅ ሄንሪ ናነን፣ለድርጅቱ ዓርማ፣ በቀይ ክብ ላይ፣ነጭ የኮከብ ምስል መቅረጽ ብቻ ሳይሆን፣ ችሎታ ያላቸውን ወጣቶች መፈለግ፣ እንዲሁም ፕሮጀክት መንደፍ.፣ከዚህም ጋር በማያያዝ ታሪከ ያቀርቡነበር። ችሎታ ያላቸው ወጣቶች ምን ለምርምር እንደሚያነሣሣቸው በመጽሔታቸው ደርዝ ባለው ሁኔታ በማቅረብ፣ «ዩገንድፎርሽት» በጀርመን ታዋቂ ተቋም እንዲሆን አብቅተዋል። ከየ፭ቱ ጀርመን ፬ቱ ዩገንድ ፎርሽትን ያውቃል። እንደ አንድ ልዩ ዓርማ የሚታይ ሆኗል።»

ወጣቶች ፤ በትርፍ ጊዜ በምርምር ላይ በማትኮር እንቅሥቃሤ በሚያደርጉበት አሠራር ፤ የተለዬ የጀርመን አያያዝ የሚመስለው ምን ይሆን?! አሁንም ዳንኤል ጊዘ--


«ጀርመንን የተለየ የሚያደርጋት፣ በአሁኑ ወቅት ከትምህርት ቤቶች ጎን-

Jugend Forscht 2013 Bundessieger Technik
ምስል Stiftung Jugend forscht e. V.

ለጎን የተማሪዎች የመርምር ጣቢያዎች እንዲደራጁ መደረጋቸው ነው። እነዚህ ተቋማት፣ወጣቶች ረዘም ላለ ጊዜ እንደ ትክክለኛ ቤተ-

ሙከራ ወይም የምርምር ማዕከል የሚጠቀሙባቸው ናቸው።

ተማሪዎችም ፕሮጀክቶችን በዚያ በመቅረጽ ለዩገንድ ፎርሽት ማመልከቻ ያስገባሉ።

ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚቀስሙት ዕውቀት ባሻገር በትርፍ ጊዜያቸው በሚያካሂዱት ምርምርበ ማትኮር ስለወደፊቱ ሙያቸውም ለዘለቄታው ሊያስቡበት ይችላሉ።

ይኸው የምርምር ጥረት የሁለተኛ ደረጃ ማለፊያ ፈተናን ከተፈተኑ በኋላ ወይም ትምህርታቸውን ከፈጸሙ በኋላ ሳይሆን

ቀደም አድርገው እንዲጀምሩ መገፋፋት ያሻል። ትምህርታቸውን ቢጨርሱም፣ይህ የኔ ምርጫ ነው፣

የምወደው የትምህርት ዓይነት ይህ ነው፤ ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ የምችለው በዚህ መስክ ነው፣

በከፍተኛ ደረጃ የማጠናውም ይህን ነው ለማለት ያስችላቸዋል።ዝንባሌን፣ችሎታን፣

አውቆ የመንቀሳቀሱ ጉዳይ ትምህርት ከማጠናቀቅ በፊት

አስቀድሞ በለጋነት መጀመር ያሻል።»

በጀርመን ሀገር ፣ ለጋ ወጣቶች ብቻ ሳይሆኑ፤ ራሱ ሕብረተሰቡም ፤ የሳይንስ ምርምር ተባባሪ በመሆን አያሌ አስገራሚ ተግባራትን እንደሚያከናውን እሙን ነው። የዜጎች ሳይንስ (ሲቲዝን ሳይንስ )በተሰኘው ንቅናቄ ፣ በተለይ የተፈጥሮ አካባቢን በማጥናትና በመንከባከብ፤ በአትክልትና አጸድ በአእዋፍ ፤ ቢራቢሮዎችና በመሳሰለው ጥናት በማካሄድና በመመዝገብ ፤ ሕዝቡ ፣ እንደ ተወዳጅና በትርፍ ጊዜ እንደሚዘወተር አዝናኝ ተግባር በመቁጠር ፣ ለሳይንስ ምርምር ሰፊ አስተዋጽዖ ያደርጋል።

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ