1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኳስ ተጫዋችነት ህልም ሲሳካ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 2 2007

በጨርቅም ይሁን በትክክለኛው ኳስ ፤ ማንኛውም ወንድ ልጅ ኳስ ተጫውቶ አድጓል ለማለት ያስደፍራል። ነገር ግን የእግር ኳስ ተጫዋች የመሆን ህልማቸውን ያሳኩ ፤ የተወሰኑ ናቸው። የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳ ከነዚህ ተጫዋቾች አንዱ ነው።

https://p.dw.com/p/1F5Py
Dawit Beshah
ምስል Fotobiniam

የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳችን የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች ነው። የ23 ዓመቱ አስቻለው፤ ኳስ መጫወት መውደዱ እና የግል ጥረቱ ዛሬ የት ደረጃ ላይ እንዳደረሰው ይናገራል።የሰራ እና የለፋ የተመኘውን ያገኛል የሚለው አስታቸለው፤ ኳስ መጫወት የጀመረው በልጅነቱ በጨርቅ ኳስ ነበር።

ወጣቱ ፤ አጥቂ፣ ተመላላሽ፣ ተከላካይ ፣ ብቻ በእግር ኳስ ህይወቱ እንዲጫወት በተመደበበት ቦታ ሁሉ እንደተጫወተ ይናገራል። ኢትዮጵያ ቡና ቡድንን የተቀላቀለውም በሌሎች ቡድኖች ውስጥ ካለፈ በኋላ ነው።ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ አልነበረም።ወጣቱ ያገኘውን አጋጣሚ ተጠቅሞ ያለውን ችሎታ ማሳየት ነበረበት። አስቻለው ኢትዮጵያ ቡናን እንደተቀላቀለም ለኢትዮጵያ ብሕራዊ ቡድን ለመመረጥ በቅቷል። ይሁንና ተቀይሮ የመግባት እና የመጫወት እድል አላገኘም።

Einführung der Torkamera
ምስል imago/Revierfoto

አስቻለው መቼ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንደሚጫወት ባያውቀውም፤ እግሩን ለአጭር ጊዜ ስላስገባበት ብሔራዊ ቡድን እንደ አንድ እግር ኳስ ተጫዋች ያለውን አስተያየት አካፍሎናል።

ወጣቱ ከእንግሊዝ ቡድኖች፤ የማንችስተርን ፤ ከስፔን ደግሞ የባርሴሎናን ቡድን ይደግፋል። ትልቅ ህልሙ ለእንግሊዝ ፕሪሜር ሊግ መጫወት ነው። የሰራ እና የለፋ የተመኘውን ያገኛል የሚል መርህ ይዞ ከሚንቀሳቀው አስቻለው ግርማ ጋር ያደረግነውን ዝግጅት በድምጭ ያገኙታል።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ