1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮንትራት ሰራተኞችን በህጋዊ መንገድ ለመላክ የተያዘው እቅድ

እሑድ፣ ጥር 17 2007

በተለያዩ መንገዶች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሃገራት ለሥራ የሚሄዱ ኢትዮጵያውን ልዩ ልዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደሚፈፀምባቸው ተደጋግሞ ሲነሳ ቆይቷል ።

https://p.dw.com/p/1EPq0
Äthiopische Flüchtlinge in Saudi
ምስል Nebiyu Sirak


በተለያዩ መንገዶች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሃገራት ለሥራ የሚሄዱ ኢትዮጵያውን ልዩ ልዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደሚፈፀምባቸው ተደጋግሞ ሲነሳ ቆይቷል ። ከ 1 ዓመት በፊት ደግሞ የሳውዲ መንግሥት ህገዊ አይደሉም ሲል ያባረራቸው ከ160 ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን አብዛኛዎቹ ባዶ እጃቸውን ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል ። በርካቶች አሁንም በሳውዲ አረቢያ ና በሌሎችም የመካከለኛው ምሥራቅ ሃገራት እንደሚንገላቱ ይሰማል ። እነዚህ ችግሮች አሁንም እንዳልተወገዱ በሚሰማበት በዚህ ወቅት ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት የኮንትራት ሠራተኞችን በህጋዊ መንገድ ወደ ውጭ ለመላክ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን አስታውቋል ። ይህን ለማሳካትም መንግሥት የዜጎችን መብትና ክብር የሚያስጠብቅ ያለውን አዲስ ህግ ማርቀቁን ብዙ ኢትዮጵያውያን ለሥራ ከሚሄዱባቸው ሃገራት መንግሥታት ጋር የሥራ ስምምነቶችን ለመፈራረም ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል ። የእንወያይ ዝግጅት የኮንትራት ሠራተኞችን ወደ ውጭ ሃገራት በህጋዊ መንገድ ለመላክ የተያዘው እቅድ ላይ ያተኩራል ።

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ