1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«የኦንላይን ሂሳብ» ሶፍትዌር ፕሮግራም

ሰኞ፣ ጥቅምት 3 2007

በዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት ፤ በግል የንግድ ዘርፍ የምትንቀሳቀስና የአንድ የሶፍትዌር ፕሮግራም ድርጅት ባለቤት የሆነች ወጣት ኢትዮጵያዊት እንግዳው አድርጓል።

https://p.dw.com/p/1DSmc
Symbolbild Rechenstreifen Rechnung
ምስል BilderBox

ባለቸው ችሎታ፣ እውቀትና ገንዘብ የራሳቸውን ስራ ለመፍጠር ከሚታትሩ ኢትዮጵያውያን ፤ አስመረት ገብረ አንዷ ናት። የ 29 ዓመቷ የሶፍትፌር ባለሙያ ባለፈው የካቲት ወር ከስራ ባልደረባዎቿ ጋር የጀመረችው የሶፍትዌር ፕሮግራም «ኦንላይን ሂሳብ» ይባላል። አስመረት ይህንኑ ፕሮግራም ለገበያ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ትገኛለች።

«ኢንቴልሲንክ» በመባል በሚጠራው የአስመረት ገብረ ድርጅት ውስጥ «የኦንላይን ሂሳብ» አንዱ የስራ ውጤት ነው። ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋሞች በእየዕለቱ የሚያደረጉትን የሂሳብ ልውውጥ ዘመናዊ በሆነ እና በቴክኖሎጂ በታቀፈ ሁኔታ እንዲገለገሉ፣ እንደ ገቢ እና ወጪ የመሳሰሉትን ከገንዘብ ጋር የተገናኙ ጉዳዮችን በቀላል መንገድ ተጠቅመው እንዲመዘግቡ ፕሮግራሙ እድል ይፈጥራል ስትል የምታብራራው አስመረት፤ ከዚህም በተጨማሪ ለምን አገልግሎት ላይ ሊውል እንደሚችል ለዶይቸ ቬለ አብራርታለች።

ፒቮት ኢስት ፤ ባለፈው ሰኔ ወር ምስራቅ አፍሪቃ ውስጥ የሚገኙ አፍሪቃውያን የስራ ፈጣሪዎች የተካፈሉበት ውድድር ነው። አስመረት ይህንኑ «የኦንላይን ሂሳብ» የፈጠራ ስራ ይዛ ናይሮቢ በተካሄደው ውድድር ስትሳተፍ ከኢትዮጵያ ብቸኛዋ አሸናፊ ናት።

በዚህ ውድድር 75 ምስራቅ አፍሪቃውያን ሲሳተፉ፤ የስራ ውጤታቸው ከፍተኛ እውቅና አግኝቶ ተሸላሚ የሆኑት 25 ብቻ ናቸው ። ከነዚህም ውስጥ 18 ኬንያውያን፣ 5 ዩጋንዳውያን ሲሆኑ ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ተሸላሚ ነበራቸው። ይኼው ውድድር በ5 ቡድን የተከፋፈለ ሲሆን፤ የአስመረት ከተሳተፈችበት የፈጠራ ስራ ቡድን ደግሞ 2ኛ ሆናለች።

ከ«ኦንላይን ሂሳብ» ሶፍትዌር ፕሮግራም ባለቤት አስመረት ገብረጋር በዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት የነበረንን ቆይታ ከዚህ በታች በድምፅ ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሰ