1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢድ አል ፈጥር በዓል አከባበር

ሰኞ፣ ሐምሌ 21 2006

የ1435ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ዛሬ በመላው የኢትዮጵያ ሙስሊም ምዕመናን ዘንድ ሲከበር ውሏል። ደማቅ አከባበር በሚደረግበት በአዲስ አበባ ስታዲዮም እና አካባቢውም እንደወትሮው የበዓሉ ሥነ ሥርዓት ሲከናወን ተስተውሏል።

https://p.dw.com/p/1Ckpn
Eid Al Fitr in Äthiopien
ምስል DW/G. Tedla

ከወትሮው ትንሽ ለየት ያደረገው ግን ፍተሻ የተጠናከረበት እና ወደ ስታድዮም ዘልቆ መግባት ለሚፈልግ ጋዜጠኛ ልዩ ባጅ ማስፈለጉ ነበር። ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ወደ ውስጥ ባይገባም የበዓሉን ሥነ ሥርዓት በቅርበት ተከታትሏል። ሌላው ወኪላችን ዮሀንስ ገብረ እግዚአብሔር ደግሞ በዓሉን በአዲስ አበባ ስታዲዮም እና በየመስጊዶች አክብረው ወደየቤታቸው ከተመለሱ ሙስሊሞች ዘንድ ጎራ ብሎ ነበር። እንዲሁ በዮናይትድ ስቴትስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችም የዛሬውን የረመዳን ጾም ፍቺ በዓል እጅግ በደመቀ ሁኔታ እያከበሩት ይገኛሉ። ኢትዮጵያዊው የሙስሊም ማኅበረሰብ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች በገዛቸው መስጊዶችና በተለያዩ አዳራሾች በመታደም ዕለቱን በተለያዩ ሥነ ሥርዓቶች አክብሯል። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ልኮልናል። ከዚህም ሌላ በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በዓሉን እንዴት እንዳከበሩ በቅደም ተከተል ከቀረቡት የድምፅ ከገባዎች ያገኛሉ።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ ዘገባዎች አሳይ