የኢትዮጵያዊዉ አዳጊ የነፃ ትምህርት እድል
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 1 2006ማስታወቂያ
ኢትዮጵያዊዉ አዳጊ ይስሃቅ አይሪስ ወደተባለዉ ኢተን ኮሌጅ ገብቶ ለመማር የነፃ የትምህርት እድል ያገኘዉ በችሮታ ሳይሆን ለትምህርት በሰጠዉ ሰፊ ትኩረት እና ጥረቱ ነዉ። ይስሃቅ ብሪታንያ ተወልዶ ቢያድግም በቤተሰቡ ቋንቋ ሃሳቡን አጣፍጦ ይገልፃል። አነጋገሩም የማስተዋል አቅሙን ያመለክታል። አዳጊዉ ተወልዶ ያደገዉ በብሪታንያ በድህነታቸዉ ከታወቁ የመኖሪያ አካባቢዎች በአንዱ መሆኑን ከሎንዶን የተላከዉ የሃና ደምሴ ዘገባ ያመለክታል።
ሃና ደምሴ
ሸዋዬ ለገሠ
ሂሩት መለሰ