1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያና የጀርመን የረዥም ዘመናት ግንኙነት

ሰኞ፣ ኅዳር 1 2007

ኢትዮጵያና ጀርመን ዘመናት የተሻገረ የሁለትዮሽ ግንኙነት በመካከላቸዉ የመሠረቱ ሃገራት መሆናቸዉ በመረጃዎች የተመዘገበ ነዉ። ሁለቱ ሃገራት ይፋዊ የዲፕሎማሲ ዉል ከተፈራረሙም 105 ዓመታት ተቆጥረዋል።

https://p.dw.com/p/1DjAZ
Äthiopischer Kaiser Haile Selassie zu Besuch in Bonn 1973
ምስል picture alliance/AP/Hinninger

በእነዚህ ጊዜያትም አንደኛቸዉ ለሌላቸዉ የድጋፍና እርዳታ እጃቸዉን የዘረጉባቸዉ ወቅቶች በታሪክነት ተመዝግበዋል። ጀርመን በተባበሩት ኃይሎች ተቀጥቅጣ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት ባቀረቀረችበት ወቅት ምዕራብ ጀርመንን በይፋ በመጎብኘት አጋርነቷን ያሳየች ሀገር ኢትዮጵያ ናት። አጼ ኃይለ ሥላሴ ይህን ታሪካዊ ጉብኝት ካደረጉም ጥቅምት 29 ቀን 2007ዓ,ም 60 ዓመት ሞላዉ። ያኔ ንጉሡ ባዶ እጃቸዉን አልነበረም ወደተጎዳችዉ ጀርመን የመጡት የብርድ ልብሶች፤ ምግብና ገንዘብ ረድተዋል። ዶቼ ቨለ ይህን ወቅት ተንተርሶ የጀርመንና ኢትዮጵያን ግንኙነት በሚመለከት ዉይይት አካሂዷል። ሙሉ ዉይይቱን ከድምጽ ዘገባዉ ያገኙታል።

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ