1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያና የቻይና ንግድ ግንኙነት

ረቡዕ፣ ሐምሌ 23 2006

የኢትዮጵያ እና የቻይና ግንኙነት ረዘም ያለ ዘመናትን ያስቆጠረ ነው። የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት የበለጠ የተጠናከረው እና የዛሬ መልኩን የያዘው ግን ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ነው።

https://p.dw.com/p/1CmYU
China Einfluss in Afrika Baustelle in Addis Abeba Äthiopien
ምስል Getty Images

የኢትዮጵያና የቻይና ንግድ ግንኙነት

የኢትዮጵያ እና የቻይና ግንኙነት ረዘም ያለ ዘመናትን ያስቆጠረ ነው። የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት የበለጠ የተጠናከረው እና የዛሬ መልኩን የያዘው ግን ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ነው። የሁለቱ ሃገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ያደረጓቸው ተከታታይ ጉብኝቶች እና ውይይቶችም የንግድ፤ ኢኮኖሚና ቴክኒካዊ ድጋፍ ስምምነቶች በመፈራረም የተቋጩ ነበሩ። ስለ ሁለቱ ሃገራት የንግድ ግንኙነት እሸቴ በቀለ ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅሮዋል።

በኢትዮጵያና ቻይና መካከል ያለው ግንኙነት ስልጣን ላይ ካሉት ፓርቲዎች ጀምሮ የተዘረጋ ነው።የንግድ ግንኙነቱ ግን ሁለቱን ሃገራት በፍትሃዊነት ተጠቃሚ ያደረገ አይደለም። በአለም የገንዘብ ተቋም መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ እኤአ በ2004 ዓም ከቻይና የ291 ሚሊዮን ዶላር እቃ ስታስገባ ወደ ቻይና ከላከችው ያገኘችው 16 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነበር። ይህ የንግድ ሚዛን መዛባት በ2011 ዓምም ለውጥ አላሳየም። በአመቱ በሁለቱ ሃገሮች መካከል የተካሄደው ግብይት በ722 ሚሊዮን ዶላር ለቻይና ያደላ ነው።በቦን ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙት አቶ አሌክሳንደር ደምሴ በሚቀጥለው አመት ወደ ሦስት ቢሊዮን ዶላር የማሳደግ እቅድ እንዳለ ይናገራሉ።

ዛሬ ሁጂያን የጫማ ፋብሪካን ጨምሮ በርካታ የቻይና ኩባንያዎች ርካሽ የሰው ጉልበት ፍለጋ በአፍሪካ ከሚመርጧቸው የአፍሪካ ሃገራት ኢትዮጵያ አንዷ ሆናለች። የቻይና ኩባንያዎች በተከዜና ግልገል ጊቤ ሶስት የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ውስጥ በገንዘብ ድጋፍ ፤ በግንባታና ቁሳቁስ በማቅረብ ተሳታፊ ናቸው። በኢትዮጵያ የቴሌኮምዩንኬሽን፤ መንገድና የባቡር መንገድ ዝርጋታ ውስጥ የቻይና ተሳትፎ ሁሉን አቀፍ ነው። እናም ዛሬ በኢትዮጵያ የቻይና ድምጽ ጎልቶ ይሰማል። የኩባንያዎቹ ፈርጣማ ክንድ ለኢትዮጵያ ነጋዴዎች፤ ኩባንያዎችና ባለሙያዎች የሚፈጥረው ጫና ይኖራል።

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ