1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ-ጀርመን የምርምር እና የባህል ልዉዉጥ

ሐሙስ፣ መስከረም 22 2007

በጀርመን እና በኢትዮጵያ መካከል፤ ያለዉ የትምርት የምርምር እና የባህል ልዉዉጥ ግንኙነት እጅግ የቆየ መሆኑ ይታወቃል። በተለይ ከጎርጎረሳዉያኑ 1624 እስከ 1704 ከኖረዉ ጀርመናዊ ምሁር ሂዮብ ሩዶልፍ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያሉ ምሁራን በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ጥንታዊ ቅርሶች፤

https://p.dw.com/p/1DOr1
Beuth Hochschule für Technik Berlin Projekt "East African UniGI Community"
ምስል DW/A. Tadesse-Hahn

የብራና መጻሕፍት የቋንቋ የባህል የታሪክ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ምርምርና ጥናት ስራቸዉ ይታወቃል። ይህ የምርምርና የባህል ልዉዉጥ የበለጠ እንዲልቅ በማሰብ ከጥቂት ዓመታት በፊት ጥናቱ በሁለቱም ሀገራት ላይ እንዲቀጥል የሀምቡርግ የባሕር ዳር እንዲሁም ደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲዎች የምርምር ስራዎቻቸዉን ለመለዋወጥ እና ተማሪዎች በሁለቱም ሀገራት ልምዶችን እንዲቀያየሩ ለማስቻል «ዓባይ የጥናት የምርምር ማዕከል» በሚል ባህር ዳር ዩንቨርስቲ ላይ ማዕከል ተቋቁማል። በለቱ ዝግጅታችን የዚህ ማዕከል መስራች በሐንቡርግ ዩንቨርስቲ ዶክተር ጌቴ ገላዩ እንዲሁም ሰሞኑን ለሥራ ጉብኝት ወደ ጀርመን በርሊን የመጡት በባህር ዳር ዩንቨርስቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ተስፋዬ ሽፈራዉን የለቱ ዝግጅታችን እንግዶች አድርገናል።
ለአራት ቀናት ስብሰባ ወደ ጀርመን መዲና በርሊን የመጡት በባሕር ዳር ዩንቨርስቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ተስፋዬ ሽፈራዉ፤ የማስተርና የዶክትሬት ማዕረግ ትምህርታቸዉን የተከታተሉት በዚሁ በጀርመን እንደሆነ ይናገራሉ፤ በርሊን ላይ የመጡበትንም ስብሰባ አጠናቀዉ ነገ ወደ ኢትዮጵያ ተመላሽ ናቸዉ ።
የባሕር ዳር ዩንቨርስቲ ከከሀንቡርግ ዩንቨርስቲ ጋር በተለይ በባህል በቋንቋ ጥናት ላይ እንደሚሰራ ዶክተር ተስፋዬ ገልፀዉልናል።
በባሕርዳር የፎክሎር ወይም የባሕል ጥናት ቅድመ ምረቃ መረሃ-ግብር እንዲጀመር እንዲሁም ከጀርመናዉያን ብሎም ከሌሎች የአዉሮጳ ሀገራት ምሁራን ጋር የታሪክ የባህል የቋንቋ የቅርስ የጥናት እና የምርምር ስራን መለዋወጥ ይቻላል በሚል በባሕርዳ ዩንቨርስቲ «ዓባይ የጥናት የምርምር ማዕከል»ን ያቋቋሙት በሐምቡርግ ዩኒቨርሲቲ የእስያና የአፍሪቃ ጥናት ተቋም ውስጥ የአፍሪቃና የኢትዮዽያ ጥናቶች ትምህርት ክፍል የአማርኛ ቋንቋና የአፍሪቃ ፎክሎር እንዲሁም ሥነ-ቃል መምህር ዶክተር ጌቴ ገላዬ፤ እንዳሉት «ዓባይ የጥናት የምርምር ማዕከል «ዳይሪክተር ተሾሞለታል፤ በማዕከሉ ወጣት ተመራማሪዎች እንዲሰሩ እንዲመደቡ ተደርጎአል። ወጣት ተመራማሪዎቹ ከሌሎች የኢትዮጵያ ዩንቨርስቲ ምሁራን ጋር እንዲሰሩና ልምድ እንዲካፈሉም ተደርጎአል። ,,,» ዶክተር ጌቴ ማዕከሉ የተደራጀ ቤተ-መጻህፍት በቁሳቁስ እና የምርምር ማመሳከርያ መጻሕፍት የጥናት ጽሑፎች እጥረት እንዳለበት ሳይገልፁ አላለፉም።
ለሥራ ጉዳይ ወደ ጀርመን መጥተዉ መዲና በርሊን ላይ ያገኘናቸዉ በባህር ዳር ዩንቨርስቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ተስፋዬ ሽፈራዉ እንደሚሉት « በዩንቨርስቲያችን በባህል ዙርያ በማኅበረሰብ ጥናት ዙርያ በተለያየ መልኩና በተለያየ መጠን እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ቢኖሩም ምናልባት በዉጭ የሚገኝዉ ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ ሊያበረክት የሚችለዉን አስተዋፆ እንዲገልፅ እያሳሰብን፤ በኛ በኩል ከቅርስ፤ ከታሪክ ከባህል፤ ቋንቋ ጋር በተያያዘ መድረኮችን በተለያየ ግዜ እንንፈጥራለን ሀገር አቀፍ አዉደ ጥናቶችን በተለያዩ ግዝያቶች እናካሂዳለን።»
ለባህል ጥናት ለቅርስ ጥበቃና ቱሪዝም እድገት ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለዉ ስለተነገረለት የባህር ዳሩ «ዓባይ የጥናትና የምርምር ማዕከል» እንዲሁም ስለ ኢትዮጵያ ጀርመን የባህል ልዉዉጥ ማብራርያ የሰጡንን የዕለቱን እንግዶቻችንን እያመሰገንን ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።


አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ

Mutter und Sohn Tannasee Baher Dahr Äthiopien
ምስል DW/A. Tadesse-Hahn
Beuth Hochschule für Technik Berlin Projekt "East African UniGI Community"
ምስል DW/Azeb Tadesse Hahn