1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃዉያን የግል ተቋማት በጀርመን

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 4 2007

በርካታ አፍሪቃዉያን ወደ አዉሮጳ ለመሰደድ በባሕር ሙከራ ሲያደርጉ ብዙዎች ሰምጠዉ የደረሱበት እንኳ የማይገኘዉ ቁጥራቸዉ የትየለሌ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1DVRC
Luisa Joao Pedro in ihrem Afroshop
ምስል DW/C.Fenandes

ይህን የባሕር ላይ አደጋ በእድል አልፈዉ በአዉሮጳ የጥገኝነት ኑሮን ሲጀምሩ ደግሞ፤ ብዙ መከራና ስቃይ የሚያዩ ብዙዎች ናቸዉ። ይህን መከራና ስቃይ አልፈዉ ቋንቋ ተምረዉ ሥራን የሚያገኙ ከዝያም አልፎ የራሳቸዉ የንግድ ተቋማት ለማቋቋም እድል የሚገጥማቸዉም ይገኛሉ። በጀርመን የሚኖሩ አፍሪቃዉያን የግል ተቋሟት በብዛት ከሚገኝባቸዉ ከተሞች ደግሞ ፍራንክፈርት ከተማ ትጠቀሳለች። ፍራንክፈርት አካባቢ ነዋሪ የሆነዉ ተባባሪ ዘጋብያችን ጎይቶም ቢሆን ዛሬ በጀርመንና አዉሮጳ ዝግጅት ፍራንክፈርት ከተማ ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያዉያን የንግድ ተቋማትን ቃኝቶ ዘገባ ልኮልናል።

ጎይቶም ቢሆን
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ