1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ ዓመት ክብረ በዓል ወግ

ሐሙስ፣ መስከረም 1 2007

እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ ፤ እንቁጣጣሽ በየዓመቱ ያምጣሽ ብለናል በድጋሚ፤ ለመሆኑ የዘመን መለወጫ እንቁጣጣሽ ትርጉሙ ምን ይሆን ፤ በክብረ በዓሉ ወቅት የሚከናወኑትስ ሃይማኖታዊ ባህላዊ ማህበራዊ ክንዋኔዎችስ እንዴት ይታያሉ፤

https://p.dw.com/p/1DAck
ምስል DW/A. Tadesse-Hahn

በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የትያትር ጥበባት፤ መምህርና የድህረ ምረቃ ፕሮግራም ተባባሪ ዲን አሰፋ ወርቁ ጥሩነህ በሶስት የተለያዩ ዘመናት የወጡ መዝገበ ቃላቶች አገላብጠዉ የእንቁጣጣሽን ትርጉም በተለያየ መንገድ ይፈቱታል።
በሀገራችን የሚከበረዉ እንቁጣጣሽ የአዲስ ዓመት ክብረ-በዓል ሀይማኖታዊ ባህላዊ ባዕድ አምልኮታዊ ባህሪ ያለዉ ከሌሎች በዓላት ሁሉ ለየት ያለ ክብረ በዓል ነዉ ሲሉ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህሩ አሰፋ አሰፋወርቁ ጥሩነህ ገልፀዉልናል። በአዲስ ዓመት ዋዜማ በተለይ በከተማ አካባቢ ችቦ ይበራል፤ የችቦ ትርጉሙ ምን ይሆን በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የቋንቋ ክፍል መምህር መስፍን መሰለ እንደሚሉት የብሩህ ተስፋ ምልክት ነዉ። አዲስ ዓመት ፤ ዘመን መለወጫ፤ ማኅበረሰቡን የሚያቀራርብ ሰላም የሚያነግስ ፍቅር እና የጥሩ ምኞት መለዋወጫ ማህበራዊ ባህሪ ያለዉ ተወዳጅ በዓል መሆኑን በስፋት ያብራሉልን የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህራን ሙሉ ቃለ-መጠይቅ የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ።
አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ