1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ፓርላማና የአርመኖች ጭፍጨፋ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 8 2007

የአርመን መንግሥት ውሳኔውን አወድሶ እርምጃው በሁለቱ ሃገራት መካከል እርቀ ሰላም እንዲወርድ መንገድ ጠራጊ እንደሚሆንም አስታውቋል ። ቱርክ የዛሬ መቶ ዓመት ከአርመን ጋር በተካሄደው ውጊያ በርካታ አርመናውያን መገደላቸውን ታምናለች ። ሆኖም ያኔ የርስ በርስ ጦርነት እንጂ የዘር ማጥፋት ወንጀል አልተፈጸም ስትል ነው የምትከራከረው ።

https://p.dw.com/p/1F9Yk
Brüssel Mitglieder Europäisches Parlament Schweigeminute Armenien Völkermord
ምስል Reuters/F. Lenoir

የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ኦቶማን ቱርክ በአርመናውያን ላይ የፈፀመው ጭፍጨፋ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው ሲል ትናንት በአብላጫ ድምፅ ያሳለፈው ውሳኔ አርመንን ሲያስደስት ቱርክን ደግሞ አስከፋ ። ፓርላማው በጉዳዩ ላይ ድምፅ ከሰጠ በኋላ የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ የአውሮፓ ፓርላማ ሌላ ታሪክ ለመፃፍ እየሞከረ ነው ሲል ወቅሷል ። ከውሳኔው በፊት የቱርክ ፕሬዝዳንት ታይፕ ኤርዶጋን ውሳኔውን ከቁም እንደማይቆጥሩት ተናግረው ነበር ። የአርመን መንግሥት ውሳኔውን አወድሶ እርምጃው በሁለቱ ሃገራት መካከል እርቀ ሰላም እንዲወርድ መንገድ ጠራጊ እንደሚሆንም አስታውቋል ። ቱርክ የዛሬ መቶ ዓመት ከአርመን ጋር በተካሄደው ውጊያ በርካታ አርመናውያን መገደላቸውን ታምናለች ። ሆኖም ያኔ የርስ በርስ ጦርነት እንጂ የዘር ማጥፋት ወንጀል አልተፈጸም ስትል ነው የምትከራከረው ። የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ ዝርዝሩን ልኮልናል ።

ገበያው ንጉሴ

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ