1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ሕብረትና የቱርክ ግንኙነት

ማክሰኞ፣ ኅዳር 30 2007

ሕብረቱ ባለሥልጣናቱን ወደ አንካራ የላከዉ ቱርክን ከሩሲያ «ለመሻማት ነዉ»-የሚል አስተያየት አስከትሏል። ወይዘሮ ፌሬደሪከ ግን የጉብኙቱ ዓላማ ከዩክሬን ቀዉስ በተጨማሪ የተቋረጠዉ የቱርክና የሕብረቱ የአባልነት ድርድር ስለሚቀጥልበት ሁኔታ፤የሶሪያ ስደተኞች፤በISIS ላይ የተከፈተዉ ዘመቻንም ይጨምራል ባይ ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/1E1Zm
ምስል picture-alliance/AA/Y. Bulbul

የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ግንኙነት ሐላፊ ወይዘሮ ፌሬድሪከ ሞጌሪኒ የመሩት የሕብረቱ የመልዕክተኞች ቡድን ቱርክን ለሁለት ቀን ጎብኝቷል። ከሩሲያ ጋር የዲፕሎማሲና የምጣኔ ሐብት ጦርነት የገጠመዉ የአዉሮጳ ሕብረት ከፍተኛ ባለሥልጣናቱን ወደ አንካራ የላከዉ የሩሲያዉ ፕሬዝንት ቭላድሚር ፑቲን አንካራን በጎበኙ ማግሥት መሆኑ ነዉ። በዚሕም ሰበብ ሕብረቱ ባለሥልጣናቱን ወደ አንካራ የላከዉ ቱርክን ከሩሲያ «ለመሻማት ነዉ»-የሚል አስተያየት አስከትሏል። ወይዘሮ ፌሬደሪከ ግን የጉብኙቱ ዓላማ ከዩክሬን ቀዉስ በተጨማሪ የተቋረጠዉ የቱርክና የሕብረቱ የአባልነት ድርድር ስለሚቀጥልበት ሁኔታ፤የሶሪያ ስደተኞች፤ በISIS ላይ የተከፈተዉ ዘመቻንም ይጨምራል ባይ ናቸዉ። የብራስልስ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ