1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ

ዓርብ፣ የካቲት 6 2007

መሪዎቹ ከዚሕም በተጨማሪ ሥለግሪክ የምጣኔ ሐብት ቀዉስ፤ በተጠርጣሪ አሸባሪዎች ላይ መንግሥታቱ ሥለሚያደርጉት ቁጥጥርም ተነጋግረዉ።አዉሮጳ መድረሻ ሜድትራንያን ባሕር ዉስጥ የሚረግፉት የአፍሪቃዉያን ስደተኞች እልቂት ግን በሕብረቱ መሪዎች ዘንድ ከቁብ አልተቆጠረም

https://p.dw.com/p/1EbSS
ምስል Emmanuel Dunand/AFP/Getty Images

የዩክሬን ተፋላሚ ሐይላትና የየተፋላሚዎቹ ደጋፊዎች ትናንት ሚኒስክ-ቤላሩስ ዉስጥ የተፈራረሙት የሠላም ዉል ገቢራዊነቱ ብዙ እያነጋገረ ነዉ።ትናንትናዉኑ ብራስልስ-ቤልጅግ ተሰብሰበዉ የነበሩት የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት መሪዎች ለስምምነቱ መፈረም የጣሩትን የጀርመንና የፈረንሳይ አቻዎቻቸዉን አንድንቀዉ ሥምምነቱን አወድሰዉታል።መሪዎቹ ከዚሕም በተጨማሪ ሥለግሪክ የምጣኔ ሐብት ቀዉስ፤ በተጠርጣሪ አሸባሪዎች ላይ መንግሥታቱ ሥለሚያደርጉት ቁጥጥርም ተነጋግረዉ።አዉሮጳ መድረሻ ሜድትራንያን ባሕር ዉስጥ የሚረግፉት የአፍሪቃዉያን ስደተኞች እልቂት ግን በሕብረቱ መሪዎች ዘንድ ከቁብ አልተቆጠረም።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ አጭር ዘገባ አለዉ።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ