1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተፈጥሮ ሀብት ፣ የሥነ ቴክኒክ ሽግግርና ዕድገት

ረቡዕ፣ መጋቢት 30 2007

በዓለም ዙሪያ የተፈጥሮ ሀብት ፤ በሰፊውና በመጠኑ የታደሉ ሃገራት ጥቂቶች አ,ይደሉም፣ ከሞላ ጎደል ምንም የሌላቸውም አሉ።

https://p.dw.com/p/1F1AS
ምስል Reuters

በማስተዋል በሚነደፍ የአጭር ጊዜና የረጅም ጊዜ እቅድ ፣ የተፈጥሮ ሃብትን ለህዝብ ጠቀሜታ እንዲውል የሚያደርጉ መንግሥታት የመኖራቸውንያህል፤ ሰፊው ሕዝብ አንዳች ጥቅም ሳያገኝ፤ ጥቂት የአገዛዝ ሥርዓት ቁንጮ አባላትና የውጭም የውስጥም ተባባሪዎቻቸው ብቻ ሲንደላቀቁበት ማየት በዓለማችን አዲስ ርእይ አይደለም። ለምሳሌ ፤ ከአፍሪቃው ክፍለ ዓለም ፤ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክን፤ የአንጎላን የናይጀሪያንና የመሳሰሉ አገሮችን ሕዝቦችና የገዥዎች የኑሮ ይዞታ መመልከት ይቻላል።

ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜያት ለውጭ ገበያ ሊቀርብ የሚችል የከርሠ-ምድር ሃብት እንዳላት ቢነገርም ፣ በዚህ ረገድ በተጨባጭ ሁኔታ ጎልቶ የታየ የለም። ይሁንና ፤ እ ጎ አ በ 2017 ፤ ማለትም በ 2 ዓመት ገደማ ውስጥ ፣ የተፈጥሮ ጋዝ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ በጉጉት ላይ እንደምትገኝ ፣ ጠ/ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ ባለፈው ዓርብ መግለጣቸው የሚታወስ ነው። ይህ በሳይንስና ቴክኖሎጂ እገዛ የተገኘው የተፈጥሮ ሀብት የሆነ ንጥረ ነገር ፣ ለአንድ ሀገር ምን ዓይነት ትርጉም እንዳለው በኢትዮጵያ የኮሙዩኒኬሽን ሚንስቴር ፤ ሚንስትር ደኤታ እውነቱ ብላታ ያስረዳሉ--

ተክሌ የኋላ

ኂሩት መለሰ