1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተገታተሩ ደም ሥሮች/ሔሞሮይድስ

ማክሰኞ፣ የካቲት 24 2007

ኪንታሮት በተለያዩ የሰዉነት ክፍሎቻች ላይ የሚወጣ ከቆዳ በሽታዎች አንዱ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ። መነሻ ምክንያቱ ደግሞ ቫይረስ ወይም ተሐዋሲ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1Ejym
Filmstill Feuchtgebiete
ምስል Peter Hartwig/Majestic

ከዚህ ሌላ በሰገራ መዉጫ ወይም ፊንጢጣ ላይ የሚወጣዉም በተለምዶ ኪንታሮት የሚባል አለ። የሕክምና ባለሙያዎች ግን ይህ አጠራር ለበሽታዉ በእንግሊዘኛ የተሰጠዉን ስያሜ ሄሞሮይድስን በትክክል እንደማይወክል ያስረዳሉ። ይህ ማለት የተገታተሩ ደምስሮች ማለት ነዉ። መንስኤዉ ምንድነዉ መፍትሄዉስ? በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በቀዶ ህክምና ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑትን ዶክተር አበበ በቀለን ያብራሩታል። እሳቸዉ እንደገለፁትም አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ላይ በሚሆንበት ጊዜ ህክምናዉ ቀላል ነዉ። ሶስተኛዉ ደረጃም እንደባለሙያዉ አገላለፅ ያን ያህል ከባድ የሚባል አይደለም። አራተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ ግን የቀዶ ጥገና ህክምና ማግኘቱ የግድ ነዉ። ለመሆኑ በፊንጢጣ አካባቢ የሚወጠረዉና የሚወጣዉ የደም ስር ወይም ሂሞሮይድስ ብዙ ይሆን? ዶክተር አበበ ያስረዳሉ።ይህ የጤና ችግር ሲገጥመዉ አንድ ሰዉ በግሉ ምን ማድረግ ይችላል? እንዳይከሰትስ? ዶክተር አበበ በቀለ ይመክራሉ፤ ከድምፅ ዘገባዉ ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ