1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቃዋሚዎቹ ጠበቃ ተደበደቡ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 1 2007

ደብዳቢዉ ከአቶ ተማም ጋር አብሮ በነበሩና ባካባቢዉ ሰዎች ትብብር ተይዞ ሲጠየቅ የአዕምሮ በሽተኛ ይመስል የተለያዩ ፖለቲካዊ ርዕሶችን እያነሳ ይናገር እንደነበር የዓይን ምስክሮች አስታዉቀዋል።

https://p.dw.com/p/1EoH9
ምስል fotolia

የኢትዮጵያ መንግሥት አሸባሪነትን ጨምሮ በተለያዩ ወንጀሎች ለከሰሳቸዉ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፤ የሐይማኖት መሪዎችና ጋዜጠኞች ጥብቅና በመቆም የሚታወቁት አቶ ተማም አባ ቡልጎ ተደበደቡ።አቶ ተማም የተደበደቡት ዛሬ ከችሎት ወጥተዉ በመኪና ሲጓዙ ነዉ።ደብዳቢዉ ከአቶ ተማም ጋር አብሮ በነበሩና ባካባቢዉ ሰዎች ትብብር ተይዞ ሲጠየቅ የአዕምሮ በሽተኛ ይመስል የተለያዩ ፖለቲካዊ ርዕሶችን እያነሳ ይናገር እንደነበር የዓይን ምስክሮች አስታዉቀዋል።አቶ ተማም አይናቸዉ አካባቢ መጠነኛ ጉዳት ቢደርስባቸዉም ለክፉ የሚሰጥ አይደለም።ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ