1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተመድ ባለስልጣናት የስደተኞች ጉብኝት በጋምቤላ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 15 2006

በደቡብ ሱዳን ጦርነት ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱ ተፈናቃዮች ቁጥር ከ200,000 በላይ መድረሱ ተነግሯል። ስደተኞቹ በተለይ ወደ ጋምቤላ የፈለሱ ሲሆን፤ የሚገኙበት ሁናቴ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን በተመድ የሠብዓዊ ርዳታ አስተባባሪ በእንግሊዘኛ ምኅፃሩ ኦቻ ዋና ዳይሬክተር ጆን ጊንግ አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/1Cgow
ምስል Reuters

ጋምቤላ የሚገኙትን እነዚህኑ ስደተኞች የጎበኙት የዓለም የምግብ ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ አብዱ ዲያንግ እና የብሔራዊ ቀይ መስቀል ዋና ፀሐፊዋ ወ/ሮ ፍሬሕይወት ወርቁ በዚያ የተመለከቱትን ለዶቸቬለ ገልፀዋል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅሮ ልኮልናል።


ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሰ