1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሪታንያ ጠ/ሚንስትር ለኢትዮጵያ አቻቸው የላኩት ደብዳቤ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 18 2007

ከጥቂት ወራት በፊት ሰንዓ የመን ውስጥ ተይዘው ለኢትዮጵያ ተላልፈው የተሰጡት የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ፓርቲ ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ በተመለከተ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ካምረን ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከጥቂት ጊዜ በፊት ደብዳቤ እንደላኩ ተገልጾዋል።

https://p.dw.com/p/1DdLA
ምስል Reuters/C. Hartmann

በቅርቡ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው የተሰጡት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የት እንደታሰሩም ሆነ በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ እስካሁን በግልጽ አለመታወቁ ቤተሰቦቻቸውን እና ደጋፊዎቻቸውን አሳስቦዋል። የመን አቶ አንዳርጋቸውን ለኢትዮጵያ አሳልፋ መስጠቷን ያወገዙት የመብት ተሟጋች ድርጅቶችም አቶ አንዳርጋቸው ቁም ስቅል ሊያጋጥማቸው ይችላል በሚል ስጋታቸውን በተደጋጋሚ መግለጻቸው የሚታወስ ነው። የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ጻፉት ስለተባለው ደብዳቤ ቀደም ሲል የለንደኑን ወኪላችን ድልነሳ ጌታነህን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ድልነሳ ጌታነህ

አርያም ተክሌ

ተክሌ የኋላ