1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤልጅግ የአዲስ መንግሥት ምሥረታ

ዓርብ፣ መስከረም 30 2007

የቤልጅግ የአዲስ መንግሥት ምሥረታ፣ባለፈው ግንቦት ወር በተደረገው ምርጫ፣ አብላጫ ድምፅ ያገኙት የቤልጅግ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምር መንግሥት ለማቋቋም መስማማታቸውን አስታወቁ።ከ 135 ቀናት ውይይትና ድርድር በኋላ መንግሥት ለመመሥረት የተስማሙት የሊብራልና

https://p.dw.com/p/1DTHu
ምስል Getty Images/AFP/Belga Photo/Dirk Waem

የክርስቲያን ዴሞክራት የመኻል ቀኝ ፓርቲዎች ፣ ከ «ፍሌሚሹ» ብሔርተኛ ፓርቲ New Flemish Alliance (N-VA) ጋር በመጣመር ነው። አዲስ ጠ/ሚንስትር ይሆኑ ዘንድ የተመረጡት፣ የፈረንሳይኛው ክፍል የሊብራል ፓርቲ መሪ ምስተር ቻርለስ ሚሸል ናቸው። የ 38 ዓመቱ ጎልማሣ ቻርለስ ሚሸል፣ በቤልጅግ ፖለቲካ ብዙ ተሳትፎ ያላቸው፤ በአሁኑ ወቅትም፤ የአውሮፓ ፓርላማ አባልና የአውሮፓ አፍሪቃና ካሪቢያን አገሮች፣ የፓርላማ አባላት ቡድን ሊቀመንበር የሆኑት ፤ የምስተር ልዊ ሚሸል የመጀመሪያ ልጅ ናቸው።

ገበያው ንጉሤ

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ