1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤልጅግ የ24 ሰዓት አጠቃላይ የሥራ ማቆም አድማ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 6 2007

በቤልጅግ ፤ ሶስት ሚሊዮን ገደማ አባላት ያሏቸው ሶስት ትላላቅ የሠራተኞች ማሕበራት በጠሩት የ 24 ሰዓት የሥራ ማቆም አድማ መሠረት፤ መዲናይቱን ብራሰልስን ጨምሮ አገሪቱ በመላ የሥራ እንቅሥቃሤዋ ተገትቶ ውሏል።

https://p.dw.com/p/1E5Dp
Belgien Generalstreik 15.12.2014
ምስል DW/B. Wesel

የሕዝብ የመጓጓዣ አገልግሎት ፤ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ የበረራ እንዲሁም የወደብ አገልግሎቶች ቀጥ ብለዋል። የቤልጅጉ የሥራ ማቆም አድማ በአውሮፓና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንዲሁም ጉባዔዎች ላይ ተጽእኖ ማድረጉ አልቀረም። ስለቤልጅጉ አጠቃላይ የሥራ ማቆም አድማና ስለአውሮፓው ሕብረት የኤኮኖሚ መርሕ የቤልጅጉን ዘጋቢአችንን ገበያው ንጉሤን በስልክ አነጋግሬው ነበር።

ገበያው ንጉሤ

ነጋሽ መሀመድ