1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቡርኪናፋሶ ፖለቲካዊ ቀዉስ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 20 2007

የፕሬዝዳንቱ ዕቅድ ያስቆጣዉ በብዙ ሺሕ የሚቆጠር የሐገሪቱ ሕዝብ ከትናንት ጀምሮ ርዕሠ-ከተማ ዋጋዱጉን በሠልፍ አጥለቅልቋታል

https://p.dw.com/p/1Deh8
ምስል Getty Images/I. Sanogo

የቡርኪና ፋሶ ፕሬዝዳንት ለተጨማሪ ዘመን መግዛት እንዲችሉ የሐገሪቱ ሕገ-መንግሥት እንዲቀየር ለምክር ቤት ያቀረቡትን ረቂቅ ሰረዙ። ምዕራብ አፍሪቃዊቱን ሐገር ላለፉት 27 ዓመት የገዙት ፕሬዝዳንት ብሌዝ ኮምፓኦሬ ሕገ-መንግሥቱ እንዲቀየር የሐገሪቱ ምክር ቤት ሕዝበ-ዉሳኔ እንዲጠራ ጠይቀዉ ነበር።የፕሬዝዳንቱ ዕቅድ ያስቆጣዉ በብዙ ሺሕ የሚቆጠር የሐገሪቱ ሕዝብ ከትናንት ጀምሮ ርዕሠ-ከተማ ዋጋዱጉን በሠልፍ አጥለቅልቋታል።ተቃዋሚዉን ካደራጁት አንዱና UPR በሚል ምሕፃረ-ቃል የሚጠራዉ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ቤኔዌንዴ ስታንሲላስ ሳንካራ ፕሬዝዳንቱ ዕቅዳቸዉን ካልሰረዙ ተቃዉሞዉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስጠንቅቀዉ ነበር።

«ከሲቢል ማሕበረሰብ ቋማት እና ከሌሎች ሐይላት ጋር በመሆን ዕቅዱ እንዲሠረዝ መታገላችንን እንቀጥላለን።ዕቅዱ ለኛ ሕገ-መንግሥታዊ መፈንቅለ መንግሥት ነዉ።ፕሬዝዳንቱ ድምፅ ያልተሰጠበትን ረቂቅ ዕቅድ መሳብ አለባቸዉ።»

ተቃዉሞዉ ቀጥሎ ምክር ቤቱ ድምፅ ለመስጠት ዛሬ ከመሰብሰቡ በፊት ተቃዋሚዎቹ የምክር ቤቱን ሕንፃ በከፊል በእሳት አጋይተወቱታል።ቃጠሎዉ እንደተስማ ፕሬዝዳንቱ ዕቅዱን መሠረዛቸዉን የሐገሪቱ መንግሥት አስታዉቋል።ወደ አመፅ የተለወጠዉ ተቃዉሞ ግን እስከ አመሻሽ ድረስ አልረገበም።የቡርኪና ፋሶ የቀድሞ ቅኝ ገዢ ፈረንሳይና ዩናይትድ ስቴትስ ዋጋዱጉን የሚያብጠዉን አመፅ አሳሳቢ ብለዉታል።

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ