1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የክረምት መርሃ ግብር በይርጋለም

ዓርብ፣ መስከረም 16 2007

በይርጋለም ከተማ የሚገኘው የቤዛዊት የወጣቶች ማዕከል ባዘጋጀው የበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች የክረምት መርሃግብር የተሳተፉ ወጣቶችን እና ስራዎቻቸውን ዝግጅቱ ባጭሩ ይቃኛል።

https://p.dw.com/p/1DLXD
Karte Äthiopien englisch

ከአዲስ አበባ 300 ኪሜ በስተ ደቡብ ርቃ በምትገኘው ይርጋለም ከተማ ፤ የቤዛዊት የወጣቶች ማዕከል ይገኛል። የማዕከሉ ትኩረት በወጣቶች ላይ ሲሆን ፤ በተለይ ተማሪዎች በቂ ትርፍ ጊዜ በሚኖራቸው በክረምቱ ወቅት ለነሱ የሚሆን የሁለት ወር ስልጠና ይሰጣል። ስልጠናው በምን ላይ ያተኮረ እንደነበር የዚሁ ማዕከል መስራች እና ኃላፊ አቶ ሞላልኝ ኃይሉ ለዶይቸ ቬለ ገልፀዋል።

51 ወጣቶች በተካፈሉበት በዚሁ ስልጠና ወጣቶች ማሟላት የነበረባቸው ልዩ መስፈርት አልነበረም ይላሉ አቶ ሞላልኝ ።ወሳኙ ነገር ወጣቶቹ በስልጠናው ለመሳተፍ ፍላጎት ማሳየታቸው ነው። በዚህ የሁለት ወር ስልጠና የተካፈሉ ጥቂት ወጣቶችን እናስተዋውቃችሁ።

አቶ ሞላልኝ ይህንን ማዕከል የመሰረቱት በ1993 ዓም ነው። ከዚያን ጊዜ አንስቶ ማዕከሉ ጥሩ ደረጃ ላይ የደረሱ በርካታ ወጣቶችን እንዳፈራ ገልፀውልናል። ይህ የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የክረምት መርሃግብር ማዕከሉ ከሚሰጣቸው ስልጣናዎች አንዱ ነው።

Äthiopien kaffeebaum
የይርጋለም ከተማ በቡና ትታወቃለች።ምስል DW/A. Hahn

በይርጋለም ከተማ የሚገኘው የቤዛዊት የወጣቶች ማዕከል ባዘጋጀው የበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች የክረምት መርሃግብር የተሳተፉ ወጣቶችን እና ስራዎቻቸውን እንዲሁም የማዕከሉን መስራች እና ለረጅም ዓመታት በበጎ ፈቃደኝነት ያገለገለን ወጣት በዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት ያካፈሉንን ከድምፅ ዘገባው ማግኘት ይቻላል።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ