1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሌ-አሜሪካዉያን መያዝ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 15 2007

በዩናይትድ ስቴትስ የሶማሊያ ማሕበረሰብ የመብት ተሟጋች እንደሚሉት የሥለላዉ መስሪያ ቤት ወጣቶቹን እንዲከታተል የጠቆሙና መረጃ የሠጡት እራሳቸዉ የሶማሌ ማሕበረሰብ አባላት ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/1FDis
ምስል picture-alliance/dpa

የዩናይትድ ስቴትሱ ማዕከላዊ የምርመራ ቢሮ « ኤፍ ቢ አይ»I አሸባሪ ቡድንን ለመቀላቀል አቅደዉ ነበር ያላቸዉን ስድት ሶማሌ-አሜሪካዉያን ወጣቶችን ባለፈዉ ዕሁድ አስሯል። የ« ኤፍ ቢ አይ» ባለሥልጣንት እንዳስታወቁት ወጣቶቹ የተያዙት እራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራዉን አሸባሪ ቡድን ለመቀየጥ ወደ መካከለኛዉ ምሥራቅ ሊጓዙ ሲዘጋጁ ነዉ።በዩናይትድ ስቴትስ የሶማሊያ ማሕበረሰብ የመብት ተሟጋች እንደሚሉት የሥለላዉ መስሪያ ቤት ወጣቶቹን እንዲከታተል የጠቆሙና መረጃ የሠጡት እራሳቸዉ የሶማሌ ማሕበረሰብ አባላት ናቸዉ። የዋሽግተን ዲሲ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ