1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስዊድን የምክር-ቤት ምርጫ

ሰኞ፣ መስከረም 5 2007

በስዊድን ትናንት እሁድ በተካሄደዉ የምክር ቤት ምርጫ አዲስ የአስተዳደር ለወጥ የሚደረግበት ዉጤት ተመዘገበ። የስካንዲኒቪያዋን ሀገር ስዊድንን የሚያስተዳድር የነበረዉ የወግ አጥባቂዉ እና የለዘብተኛዉ ጥምር መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ፍሪድሪክ ራይንፌልድ ከስምንት ዓመት ሥልጣን በኋላ በምርጫዉ ተሸንፈዋል።

https://p.dw.com/p/1DCbg
Parlamentswahl in Schweden 14.09.2014
ምስል Reuters/TT News Agency/J. Ekstromer

በአንፃሩ ቀኝ ዘመሙ ኔዎ ናዚ ስረ መሰረት ያለዉና የፍልሰት ጉዳይ ላይ ጥብቅ አቋም ያለዉ ፓርቲ ሶስተኛዉ ጠንካራ ፓርቲ በመሆን የምክር ቤት ቦታን አግኝቶአል።ስዊድን ትናንት እሁድ የምክር ቤት ምርጫ ከተካሄደ በኋላ የድምፅ ቆጠራዉ ተጠናቆ ዉጤቱ እኩለ ለሊት ላይ ነበር ይፋ የሆነዉ። በምርጫዉ አሸናፊ የሆኑትና ወደዚህ ሥልጣን ለመምጣት ብዙ ግዝያትን ያስጠበቁት ጠንካራዉ ስዊድናዊ ስቴፈን ሎቨን ፤ ዉጤቱ ይፋ እንደሆነ መራጮቻቸዉን በመድረክ ላይ ወጥተዉ አመስግነዋል። ሎቨን ምናልባትም የስዊድኑ አዲስ አስተዳደር ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆኑ እንደማይቀር ተነግሮላቸዋል። የሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ አባል ስቴፈን ሎቨን በብየዳ ስራ ከፍተኛ ትምህርትን የተከታተሉና በማኅበረሰባዊ ጉዳዮች ብዙ ልምድ ያላቸዉ መሆናቸዉ ነዉ የተመለከተዉ።
« አሁን የምርጫዉ ተጠናቆአል። ሀገራችን በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ነዉ የምትገኘዉ። በመቶ ሽ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ሥራ የላቸዉም። በኤኮኖሚ እና ልማት ትብብር ድርጅት ዉስጥ ከሚገኙ ሀገራት የትምርት ቤቶች መመዘኛ ፈተናን እኛ አነስተኛ ዉጤት አሳይተን እንደ ወደቅን ያህል ማንም ሀገር አልወደቀም። ብቻ በስዊድን የሆነ ነገር ተበላሽቶአል። ዛሪ ምሽት ግን መራጭ ህዝብ ለዚህ ሁሉ መልስ ሰጥቶአል። መንገድ ተቀይሶ ለዚህ ሁሉ የሆነ ለዉጥን ማየት ይፈልጋል። ስለዚህም አሁን በስዊድን አዲስ አስተዳደር ለመመስረት እየሰራሁ ነዉ።»
ምንም እንኳ በምርጫዉ ሶሻል ዴሞክራቶች አመርቂ የሚባል ድልን ባይቀዳጁም የምርጫዉ ዉጤት ይፋ እንደሆነ የአሸናፊዎች የድል ጭብጨባ ተስተጋብቶአል። ሎቨንም ቢሆኑ የአሸናፊነትን ቦታ ይዘዉ መድረክ ላይ ሲቀርቡ ፓርቲያቸዉ ያገኘዉን የአሸናፊ ድምፅ ቁጥር ከፍ አድርገዉ መናገር አልቻሉም። የምርጫ ዉጤቱ አረንጓዴዎች እና ግራ ፓርቲዎች ጥምረት ቢፈጥሩም እንኳ ስዊድንን ለማስተዳደር የሚያበቃ አብላጫ ድምፅን አያገኙም። በዚህም በስዊድን የፖለቲካ ሁኔታዉን ከባድ ሳያደርገዉ አልቀረም። እንደ ስቴፈን ሎቨን እምነት መግባባት የሚችል ጥምር መንግሥት መመስረት ይቻላል፤
« በስዊድን መግባባት እና መደራደር የሚችል አንድ መንግሥት ለመመስረት ዝግጁ ነኝ። ከአረንጓዴዎች ጋር ጥምር መንግሥት ለመመስረት እንዲያስችለን ለንግግር ጋብዣለሁ። በማስረገጥ መናገር የምፈልገዉ ሌሎች ዴሞክራት ፓርቲዎችን ለመሳብ እጄን መዘርጋቴንም ነዉ። ጥሪዉ ግን የስዊድን ዴሞክራቶች እያሉ የሚጠሩትን ፓርቲ አባላት አይመለከትም። ከነሱ ጋር ተባብረን አንሰራም»
የስዊድንን ወቅታዊ የመንግሥት ምስረታ ፈተና ላይ የጣለዉ ይህ አይነቱ አቋም ነዉ ። የስዊድን ዴሞክራት ፓርቲ በምርጫዉ አብላጫ ድምፅን አላገኘም። በአንፃሩ ቀኝ ዘመሙ ኔዎ ናዚ ስረ መሰረት ያለዉና የዉጭ ዜጎች ላይ የጥላቻ አቋም ያለዉ የስዊድን ዴሞክራቲክ ፓርቲ 13 በመቶ የድምፅን በማግኘት ነዉ የምክር ቤት መቀመጫን ያገኘዉ። መራጩ ህዝብም ዉጤቱ ያስጨነቀዉ አይመሰልም። በዚህምየ35 ዓመቱ ጎልማሳ ፓርቲ ሊቀመንበር ጄሚየ አክሶን እጅግ የነገሱ ያህል ተሰምቶአቸዋል። የምርጫዉ ዉጤት እጅግ ከፍተኛ ድል ነዉ ሲሉ ለፓርቲ አባሉቱ ገልፀዋል።
« እጅግ ረጅም መንገድን ተጉዘናል። አሁን በስዊድን አብላጫ ድምፅን ካገኙ ጠንካራ ፓርቲዎች ሶስተኞቹ ሆነናል። በምርጫዉ የድምፅ ቁጥሩን በእጥፍ ነዉ ያሳደግነዉ። በመንግሥት ምስረታዉ ሚዛን ላይ የምንቀመጥ አስፈላጊ መሆንን ፈልገን ነበር። አሁን በዚህ ምርጫ ይህን አግኝተናል»
በስዊድን መንግሥት ምስረታ ለዉጥ መቶአል። የስዊድን ዲሞክራት ፓርቲን አመርቂ የምርጫ ዉጤት፤ የፖለቲካ ጉዳይ ምሁራዋ ስቲና ሞርያን፤ ጥምረት ለሚፈጥሩት ለቀሪዎቹ ፓርቲዎች አሰቃቂ ሲሉ ይገልፁታል። ፓርቲዉ በፍልሰት ጉዳይ ጥያቄ ነዉ በቂ የመራጭ ድምፅ ማግኘት ያልቻለዉ።
በርካታ የመራጭ ድምፅን ያጣዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ፍሪድሪክ ራይንፌልድ የሚመሩት ለብዘብተኛዉ ፓርቲ በምርጫዉ 23 በመቶ ድምፅን በማግኘት ጥምር መንግሥቱ ከስምንት ዓመት አስተዳደር በኋላ በእሁዱ ምርጫ ከስልጣኑ ተሰናብቶአል።
« ለኔ እጅግ ጥሩ ጉዞ ነበር። በዚህ የሥራ ግዝያችን ብዙ ጥሩ ነገሮች ስለፈፀምን፤ የማካፍለዉ እና የማወራዉ በርካታ ነገሮች ይኖሩኛል። አሁን ግን ይህ ጉዞ እኔን ሳያካትት ይቀጥላል። የፓርቲ ሊቀመንበርነቱን ቦታዬንም አስረክባለሁ።»
ፍሪድሪክ ራይንፌልድ ፓርቲ በምርጫዉ በቂ ድምፅን አላገኘም፤ የፓርቲዉ አባላትም በቀጣይ ማድረግ የሚችሉት ነገር የለም፤ የወግ አጥባቂዉ ፍሪድሪክ ራይንፌልድ የፖለቲካ ጉዞ በስዊድን ምዕራፉን ዘግቶአል።
ቲም ክሮን / አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ

Wahlen in Schweden Premierminister Fredrik Reinfeldt
ምስል picture-alliance/dpa
Parlamentswahl in Schweden 14.09.2014
ምስል Reuters/TT News Agency/J. Ekstromer