1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስምጥ ሸለቆው እሳተ ገሞራዎች አዲስ ጥናት

ረቡዕ፣ ጳጉሜን 5 2006

ኢትዮጵያ ፤ በአፋር ምድርና በዋናው ስምጥ ሸለቆ በዛ ያሉ የከሰሙና በአሁኑም ጊዜ ቢሆን የሚንፈቀፈቁ ፣ እቶን እሳት የሚተፉ ፣ በዛ ያሉ እሳተ ገሞራዎች ያሏት ሀገር ናት። የዓለም ባንክ በቅርቡ ያወጣው እንዲሁ በነባቤ ቃል የተመረኮዘው ዘገባው

https://p.dw.com/p/1D5us
ምስል picture-alliance/dpa

እንደሚጠቁመው በኢትዮጵያው ስምጥ ሸለቆ አካባቢ 50 ሚሊዮን ገደማ የሚሆን ህዝብ ደረጃውም ሆነ መጠኑ ለማይታወቅ የእሳተ ገሞራ አደጋ ተጋላጭ ሆኖ ይኖራል። ይሁንና ፣ ምንና መቼ ሊያጋጥም እንደሚችል ፣ በሥጋት ከመተንበይ በስተቀር በትክክል የሚያውቅ ያለ አይመስልም።

Eritrea Vulkan Nabro NASA Rauch Flash-Galerie
ምስል NASA

በኢትዮጵያው ስምጥ ሸለቆ ከዚህ ወር አንስቶ በሚመጡት አምስት ዓመታት በእቅድ መሠረት ስለሚካሄድ ጥናትና ግብ ፣ የአንድ ባለሙያ ማብራሪያ አለን።

በዛ ያሉ የውጭ ሀገራትን ተመራማሪeዎች ጭምር የሚያማልሉ የከሰሙና ያልበረዱ እሳተ ገሞራዎች መኖራቸው እሙን ነው። ኣንዳንዴ አደጋ ማስከተል መቻላቸው ብቻ ሳይሆን ፤ ሰፊ ጠቀሜታ ስለሚሰጡት እሳተ ገሞራዎች፤ ብዛትና ዓይነት ፤ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ፤ የሥነ ምድር ሳይንስ መምህር ፣ ፕሮፌሰር ገዛኸኝ ይርጉ --

ከዚህ ቀደም ከ 5 ዓመት በላይ መቅድማዊ ፕሮጀክት አፋር መስተዳድር ውስጥ ጋባሁ በተባለ አካባቢ በ 1998 (እ ጎ አ በ 2005 )በመስከረም ወር ላይ ከፍተኛ የምርምር እንቅሥቃሴ ተደርጎ እንደነበረና ያም ምርምርና ጥናት 5 ዓመት መዝለቁን ፤ ያሁን እንቅሥቃሴም የዚያ ተከታይ ፕሮጀክት መሆኑን ነው ፕሮፌሰር ገዛኸን ያስረዱን።

Äthiopien Vulkan Erta Ale Afar Region
ምስል picture-alliance/dpa

በታላቁ የምሥራቅ አፍሪቃ ስምጥ ሸለቆ ፣ እሳተ ገሞራ በያይነቱ ከፍተኛ እንቅሥቃሴ የሚያሳይበት፣ ለተመራማሪዎችም ፍንጭ የሚሰጥበት አካባቢ ወይም አካባቢዎች ቢኖሩ፤ የአፋር ኮረብቶችና የሠመጡ ደረቅ የየብስ ክፍሎች ናቸው። ለምሳሌም ያህል ከባህር ልክ በታች 120 ሜትር ገደማ የሆነውን ጨው፤ ድኝና ፖታሲየም ማዕድናት የሚገኙበትን ፤ ዳሉልን መጥቀስ ይቻላል።

ከእሳተ ገሞራ የሚገኝ እንፋሎት አንዱ የታዳሽ ኃይል ምንጭ መሆኑ የታወቀ ነው። በአነስተኛ ደረጃ የተሞከረ ቢሆንም ባለፈው ጸደይ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር 2 ቢሊዮን ዶላር የሚያስወጣ ፕሮጀክት ለማቋቋም የተስማማውን የአይስላንድ ኩባንያ መጥቀስ ይቻል ይሆናል።

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ