1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሱዳን የተቃውሞ ግንባር መሪ በበርሊን

ሰኞ፣ ጥር 18 2007

ራሱን የሱዳን ሰፊ ብሔራዊ አገር አቀፍ ግንባር ያለው በዛያሉ ፓርቲዎችን የወጣቶችድርጅቶችን እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦችንያቀፈው የሰብስቦች ግንባር(ንቅናቄ) ፕሬዚዳንት አሊሐሰን አሕመድ ሐሰኔይ በተለያዩ የምዕራብ አውሮፓ መዲናዎች በመዘዋወር

https://p.dw.com/p/1EQmb
ምስል EBRAHIM HAMID/AFP/Getty Images

ራሱን የሱዳን ሰፊ ብሔራዊ አገር አቀፍ ግንባር ያለው በዛያሉ ፓርቲዎችን የወጣቶችድርጅቶችን እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦችንያቀፈው የሰብስቦች ግንባር(ንቅናቄ) ፕሬዚዳንትአሊሐሰን አሕመድ ሐሰኔይ በተለያዩ የምዕራብ አውሮፓ መዲናዎች በመዘዋወር ከባለሥልጣናትና ከፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች ጋርሐሳብ ተለዋውጠዋል። ባለፈው ሳምንት ማለቂያ ላይ፣ ለተመሳሳይ ጉዳይ ወደጀርመን መዲና በርሊን ብቅ ብለው በነበረበት ጊዜ ስለጉበኝታቸውና ስለሚመሩት ግንባር ዓላማ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

Omar al-Bashir Präsident Sudan 05.01.2014
ምስል AFP/Getty Images

የሱዳን አገር አቀፍ የተቃውሞ ድርጅቶች ስብስብ ፕሬዚዳንትአሊሐሰን አሕመድሐሰኔይ፣ በእንግሊዝኛው Broad National Front በምሕጸሩ (ቢኤንኤፍ) የቅርብና የረጅም ጊዜመርኀ-ግብሩ፣ ራእዩም ምን እንደሆነ ነበረ በመጀመሪያ የተጠየቁት።

«ቢኤንኤፍ» እጎአ በጥቅምት ወር ሁለት ሺ አሥር ነበረ በብሪታንያ የተቋቋመው።ያቀፈውም የተለያዩ ፓርቲዎችን፣ስደተኞችን፣የፖለቲካመድረኮችን፣የወጣትድርጅቶችን እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦችን ነው።ዓላማውም እጎአ ሰኔ ሠላሣ ቀን አሥራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ፣ በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ላይ የተቆናጠጠወን ጽንፈኛ አምባገነን አገዛዝ ከምድረሱዳን እንዲወገድ ማድርግነ ው።»
በጀኔራል ዖማርሐሰን ኧል በሺር የሚመራውን፣አምባገነናዊ ነው ያሉትን አገዛዝ እንዴትነው( ቢኤንኤፍ)ማስወገድ የሚችለው? ምን ዓይነት ነው የትግል ስልቱ?
«የአምባገነኑን የጀኔራል ኢብራሂም አቡድን አገዛዝ በጥቅምት አሥራ ዘጠኝ ስልሳ ዐራት፣ከዚያም ሁለተኛውን አምባገነን አገዛዝ በአሥራ ዘጠኝ ሰማንያ አምስት በሕዝባዊንቅናቄ አስወግደናል። ሕዝብ አምባገነንን ማስወገድ ይችላል።ለዚህ ተመክሮ አለን። አገዛዙን ለማስወገድ በጦር መሣሪያ አንጠቀመምም። የሰላም ንቅናቄ ነን። በሰላማዊ መንገድ ነው ታግለን የምንጥለው።»
ደቡብ ሱዳንን እስከመገንጠል ያደረሰው ያሁኑጨቋኝና ጽንፈኛ አገዛዝ ነው በማለትየወቀሱት ሐሰኔይ፣ ሸሪያ ሳይሆን የተለያዩ የሱዳንን ባህሎችና ሃይማኖቶች የሚያከብር የሠለጠነ የሲቭል አስተዳደር ነው የምንመሠርተው ነው ያሉት። ከኢትዮጵያና ግብፅጋር ግንባሩ ስለሚኖረው ግንኙነትም እንዲህብለዋል።

«ከጎረቤቶቻችን ጋር በመላ ጠንካራ ግንኘት መመሥረት ነውየምንሻው.።ግብጻውያን የሙስሊም ወንድማማችነት ማሕበርን በመውጋት ላይ ናቸው።እነዚሁ የሙስሊም ወንድማማችነት ማሕበር አባላት ሱዳንን እንሆ ከኻያ አምስት ዓመት በላይ በመግዛት ላይ ይገኛሉ።ለግብፃውያን የሚያሠጋ ነገር የሚመጣባቸው ከካርቱም መነግሥት መሆኑን ነግረናቸዋል፣የካርቱም መንግሥት ግብጻውን የፖለቲካአፈንጋጮችን እያሠለጠነ ወደግብፅና ወደሌላው የዓለም ክፍል በ መጉዋዝ የሽብር ተግባር እንዲያከናውኑ ያሠማራቸዋል።»

Das Abkommen in Doha zwischen der sudanesischen Regierung und der Rebellengruppe Bewegung und Gerechtigkeit über ein Waffenstillstand in Darfur
ምስል AP

በዖማር ኧል በሺር የሚመራው ያሁኑ የሱዳን መንግሥት ከኢትዮጵያው የኢሕአዴግ መንግሥት ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳለው የታወቀ ነው።የእርስዎ ግንባር Broad National Front ይህን እንዴት ይመለከተዋል?

«ከኢትዮጵያውያን ጋር ያለን ግንኙነት ያማረ የሠመረ ነው። ይህም ከአፄ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ የታየ ነው። ጣልያኖች ኢትዮጵያን ሲወሩ፣ ወደ ሱዳን ነበረ የመጡት። ያኔ ስደተኞችም በሱዳን ተጠልለው ነበር። ንጉሰ ነገሥቱ ተመልሰው በዙፋናቸው እስኪቀመጡ ድረስ ሱዳናውያን ሙሉ ድጋፍ ሰጥተናል። ጃፋር ኧል ኑሜሪ ሥልጣን ላይ ሲመጡ ወደ ኢትዮጵያ ተሰደን በዚያም ተቀብለው በሚገባ አስተናግደውናል --ኢትዮጵያውያን። ለሱዳን ሕዝብ ሲሉ ነው ያን ያደረጉት። ስለዚህ፤ ከኢትዮጵያ ጋር ያለን ግንኙነት በህዝብና መንግሥት ማለፊያ ግንኙነት ላይ የተመሠረተ ነው። የኢትዮጵያና የሱዳን ሕዝብ ጥሩ ወዳጆች ናቸው። ያሁኑ የሱዳን መንግሥት የመንግሥታትና የሕዝብ ጥሩ ግንኙነት አለ ቢልም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ድሮ የነበረው ዓይነት የሠመረ ግንኙነት አልፈጠረም። » --የሱዳን ሕዝብ ፍላጎት የመንግሥት ፍላጎት አይደለም»።

በመጨረሻም ፣ የሱዳን «ሰፊ ብሔራዊ ግንባር » የተሰኘውን የሕብረት እንቅሥቃሴ ፕሬዚዳንት አሊ ማሕሙድ አሕመድ ሐሰኔን ፤ ወደ በርሊን ጎራ ያሉበት ምክንያት ፤ ምን እንደሆነ፣ ከጀርመን መንግሥትና ሕዝብ ከአውሮፓውም ሕብረት ምን እንደሚፈልጉ ጠይቄአቸው ነበር።

«በብዙ የአውሮፓ ሃገራት ፣ ብሪታንያ፤ ፈረንሳይ ፣ ኔደርላንድ እና ጀርመን ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባለሥልጣናት እንዲሁም ከፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች ጋር ተነጋግሬአለሁ። ለጀርመናውያን የሱዳንን ወቅታዊ ይዞታ አስረድተናል። ማዕራቡ ዓለም ሊያበረክት ስለሚችለው ጠቃሚ ድርሻ ተነጋግረናል። ጉዳዩ ፤ ችግሩ የሱዳናውያን ነው። ለውጥ የሚያመጡትም ያላንዳች ጣልቃ ገብነት ሱዳናውያን ብቻ ነው የሚሆኑት። ምዕራቡ ዓለም የሱዳናውያንን ሥቃይ እንዲገነዘብ ነው የምንፈልገው።

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ